በህንድ የልጅ ልጅ ሊያሳየን አልቻለም በሚል ልጃቸውን በ50 ሚሊየን ሩፒ የከሰሱ ወላጆች
ወላጆቹ ልጃቸው ካገባ 6 ዓመት ቢሞላውም አሁንም ልጅ ለመውለድ እቅድ የለውም ብለዋል

ወላጆቹ ለልጃቸው እስካሁን ላወጡት ወጪና የልጅ ልጅ ባመለውለድ ላሳደረው ጫና 50 ሚሊየን ሩፒ ካሳ ጠይቀዋል
በህንድ ኡታራክሃንድ ግዛት ውስጥ የሚኖሩ ጥንዶች የልጅ ልጅ ሊያሳየን አልቻለም ያሉት ወንድ ልጃቸው ላይ ክስ መመስረታቸው ተሰምቷል።
ህንዳውያኑ ወላጆች ልጃቸው በአንድ ዓመት ውስጥ የልጅ ልጅ እንዲያመጣላቸውአሊያም እስከሁን በእሱ ላይ ያወጡትን 650 ሺህ የአሜሪካ ዶላር እንደሚልስላቸው በሚል ነው ልጃቸውን ፍርድ ያቆሙት።
የ62 ዓመቱ አባት ፕራሳድ ሳንጄዬቭ እና የ57 ዓመቷ እናት ሳድሃና ፕራሳድ “በአእምሯችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት” አድርሷል በሚልም በልጃቸው ላይ ያልተለመደ ክስ መመስረታው ተሰምቷል።
ወላጆቹ ልጃቸው ትምህርት እንዲማር እና ስልጠና እንዲወስድ ከፍተኛ ወጪ እንዳወጡበት፣ ስራ ባጣ ሰዓት በገንዘብ እንዳገዙት እንዲሁም በፈረንጆቹ በ2016 ሲያገባ የሰርግ ወጪውን እንደሸፈኑለት ይናገራሉ።
ወላጆቹ ለልጃቸው ላደረጉለት ነገር በእርጅና ዘመናቸው በልጅ ልጅ እንዲክሳቸውቢጠብቁም ይህንን ሊያደርግ አልቻለም በሚል ወደ ፍርድ ቤት ማቅናታቸውንም ይናገራሉ።
አባት ሚስተር ሳንጄዬቭ ፐራሳድ፤ “ልጃችን ካገባ 6 ዓመት ሞልቶታል ግን እስካሁን ከባለቤቱ ጋር ልጅ ለመውለድ እቅድ የለውም” ብለዋል።
የ62 ዓመቱ ጡረተኛ አባት ሳንጄዬቭ ፕራሳድ፤ ለልጃቸው ሲሉ ያጠራቀሙትን ገንዝብ በማውጣት በአሜሪካ የአብራሪነት ስልጠና እንዲወስድ 65 ሺህ ዶላር ወጪ እንዳደረጉ እንዲሁም በጣም ቅንጡ ሰርግ እና በታይላንድ ቆንጅ የጫጉላ ጊዜ እንዲያሰልፍ እንዲሁም 80 ሺህ ዶላር ወጪ በማድረግ መኪና እንደገዙለት ይናገራሉ።
ሆኖም ግን ይህንን ሁሉ ወጪ የ35 ዓመቱ ልጃቸው እና ባለቤቱ የልጅ ልጅ ወልደው አምጥተው እንዲመልሱ ቢጠብቁም፤ ሊያሳኩ አልቻሉም ብለዋል።
“ልጃችንን ለማሳደግ ስንል ህልማችንን ገድለናል” ለትምህረቱ ወጪው ብቻ 2 ሚሊየን ሩፒ (25 ሺህ) የአሜሪካ ብድር እስከመውሰድ ደርሰናል የሚሉት ወላጆቹ፤ ልጃችን እና ባለቤቱ ግን የልጅ ልጅ ባለምስጠት አእምሯችን ላይ ጉዳት እያደረሱ ነው ሲሉም ተናግረዋል።
ወላጆቹ ጠበቃ አርቪድን ኩማር እንደተናገረው፤ ጥንዶቹ የልጃቸው ባለቤት በአንድ ዓም ውስጥ እርግዛ የልጅ ልጅ የማይሰጧች ከሆነ በልጃቸው ላይ ላወጡት ወጪ 25 ሚሊየን ሩፒ፤ እንዲሁም በአእምሯቸው ላይ ለደረሰው ጉዳት 25 ሚሊየን ሩፒ በድምሩ 50 ሚሊየን ሩፒ ካሳ እንዲከፈላቸው ጠይቀዋል።