የጤና ሚኒስቴር አሁን ላይ ያለሁ ሁኔታ ምርጫ ማከሄድ ያስችላል ማለቱን ተከትሎ ምርጫ ቦርድ ምርጫውን ለማካሄድ የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች እያከናወነ ነው
የጤና ሚኒስቴር አሁን ላይ ያለሁ ሁኔታ ምርጫ ማከሄድ ያስችላል ማለቱን ተከትሎ ምርጫ ቦርድ ምርጫውን ለማካሄድ የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች እያከናወነ ነው
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ በግንቦት የመጨረሻዎቹ ሁለት ሳምንታት አልያም በሰኔ ወር የመጀመሪያ ሁለት ሳምንታት ለማካሄድ የመነሻ ሃሳብ አቀረበ፡፡
የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ምርጫው በክረምት ወቅት እንደማይካሄድ አቅጣጫ መቀመጡን አስታውቀዋል፡፡ ቦርዱ በምርጫ ወቅት ሊኖር በሚገባው የኮቪድ 19 ጥንቃቄ ዙሪያ ከሲቪል ማህበራት እና ከመገናኛ ብዙሃን አባላት ጋር ምክክር እያደረገ ሲሆን ለምርጫው የጥንቃቄ እርምጃ ማስፈጸሚያ የሚሆን 1.1ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ገልጿል፡፡
ከታህሳስ እስከ ጥር አጋማሽ ድረስ የምርጫ አስፈጻሚዎችን ስልጠና ለመስጠት እንደመነሻ አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን ከጥር አጋማሽ እስከ የካቲት ሶስተኛ ሳምንት ደግሞ የመራጮችን ምዝገባ ለማካሄድ መታቀዱም ተጠቅሷል።
ከየካቲት መጀመሪያ እስከ የካቲት አጋማሽ የእጩዎች ምዝገባ እንዲሁም ከየካቲት አጋማሽ እስከ ምርጫው ማካሄጃ ሳምንት ድረስ ደግሞ የምርጫ ቅስቀሳ ይካሄዳል በሚል ተቀምጧል። ከምርጫው ጋር ተያይዞ የኮቪድ 19 ጥንቃቄን የሚከታተል ግብረ ሃይል እንደሚቋቋምም ተገልጿል፡፡
በኢትዮጵያ ህገመንግስት መሰረት በየአምስት አመቱ ምርጫ የሚካሄድ ሲሆን በባለፈው አመት ሊካሄድ የነበረው ምርጫ 2012 በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ሳይካሄድ ቀርቶ ነበር፡፡ መንግስትም ወረርሽኙን ለመግታት እስከ ባለፈው ነሀሴ ወር መጨረሻ ድረስ ያበቃ የአስቸካይ ጊዜ ማወጅን ጨምሮ ሌሎች እርምጃዎች እየወሰደ ቆይቷል፡፡
የጤና ሚኒስቴር አሁን ላይ ያለሁ ሁኔታ ምርጫ ማከሄድ ያስችላል ማለቱን ተከትሎ ምርጫ ቦርድ ምርጫውን ለማካሄድ የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች እያከናወነ ይገኛል፡፡