የተራዘመው የተኩስ አቁም ጊዜ በቂ አይደለም-ተመድ
አደራዳሪዋ ኳታር የአራቱ ቀን የተኩስ አቁም ስምምነቱ በሁለት ቀናት የተራዘመው ሁለቱም ኃይሎች ፍላጎት በማሳየታቸው ነው ብላለች
የጉተሬዝ ቃል አቀባይ ስቴፋኒ ዱጃሪክ ጊዜያዊ ተኩስ አቁሙን ወደ ዘላቂ ተኩስ አቁም ለመቀየር ድርድሮች መቀጠል አለባቸው ብለዋል
ተመድ በጋዛ የተራዘመው የተኩስ አቁም ጊዜ በቂ አለመሆኑን ገልጿል።
የተመድ ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በእስራኤል እና በሀማስ መካከል በትናንተናው እለት የተራዘመው ተኩስ አቁም ተስፋ ሰጭ ቢሆንም በጋዛ ያለውን የእርዳታ ፍላጎት ለማሟላት በቂ አይደለም ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
- ለሁለት ቀናት በተራዘመው የጋዛ ተኩስ አቁም ምን ይጠበቃል?
- ለግጭት ብቸኛው መፍትሄ 'ቱ ስቴት ሶሉሽን' ተግባራዊ ማድረግ እንደሆነ የአረብ ሀገራት እና የአውሮፖ ህብረት ተስማሙ
አደራዳሪዋ ኳታር የአራቱ ቀን የተኩስ አቁም ስምምነቱ በሁለት ቀናት የተራዘመው ሁለቱም ኃይሎች ፍላጎት በማሳየታቸው ነው ብላለች።
በእስራኤል እና ሀማስ መካከል ለሰባት ሳምንታት የቆየው ጦርነት ጋብ ያለው በጋዛ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከተገደሉ በኋላ ነው።
ዘላቂ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ ቢደረግም፣ ሀማስን አጠፋለሁ የምትለው እስራኤል ግን እንደማትቀበለው ስትገልጽ ቆይታለች።
የተኩስ አቁሙ መራዘም በጋዛ እርዳታ ለሚፈልጉ ሰዎች የሚደረገውን እርዳታ መጠን ለመጨመር የሚያስችል መሆኑን የገለጹት ዋና ጸኃፊው ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ህዝብ ለመድረስ ግን የሚበቃ አይደለም ብለዋል።
ተመድ እስካሁን እርዳታ እያደረሰ ያለው በግብጽ በኩል ያለውን የራፋ ድንበርን በመጠቀም ነው። ተመድ እርዳታ ለማድረሰ በእስራኤል ቁጥጥር ስር ያለውን ከረም ሻሎም ሟቋረጫን ለመጠቀም ፍላጎት አለው።
አንቶኒዮ ጉተሬዝ ይህ እንዲሆን እስራኤል ትፈቅዳለች ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
የጉተሬዝ ቃል አቀባይ ስቴፋኒ ዱጃሪክ ጊዜያዊ ተኩስ አቁሙን ወደ ዘላቂ ተኩስ አቁም ለመቀየር ድርድሮች መቀጠል አለባቸው ብለዋል።
ሰባት ሳምንታት ያስቆጠረውን ጦርነት ያስቆመውን ጊዜያዊ ተኩስ አቁም፣ በሀማስ እጅ የነበሩ በርካታ የእስራኤል ታጋቾች እንዲለቀቁ እና በእስር ላይ የነበሩ ፍልሴጤማውያን እንዲለቀቁ አስችሏል።