ከ80 ሚሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያለው የአሜሪካው ኤፍ-35 የጦር አውሮፕላን ተከሰከሰ
ተመሳሳይ የጦር አውሮፕላን ሲከሰከስ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው ተብሏል
የአውሮፕላኑ አብራሪ ከመከስከሱ በፊት ራሱን ከአደጋው አድኗል
ከ80 ሚሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያለው የአሜሪካው ኤፍ-35 የጦር አውሮፕላን ተከሰከሰ።
የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው አሜሪካ በአላስካ ዘመናዊ የጦር አውሮፕላን ጣቢያ አላት።
ኤሊሰን በተሰኘው በዚህ የአየር ሀይል ጣቢያ ውድ እና ዘመናዊ የሚባሉ የጦር አውሮፕላኖች ይገኛሉ።
ከነዚህ ሙካከልም 54 ኤፍ-35 የተሰኘው ዘመናዊ የጦር አውሮፕላን ለብሔራዊ ግዳጅ ዝግጁ ተደርገዋል።
አንዱ ኤፍ-35 የጦር አውሮፕላን ልምምድ እያደረገ እያለ ተከስክሶ በእሳት መያያዙን ኤፒ ዘግቧል።
ይህን የውጊያ አውሮፕላን ልምድ ባለው በተባለ አብራሪ የተለመደ እና መደበኛ የውጊያ ልምምዱን እያደረገ እያለ ችግር እንደገጠመው ተገልጿል።
አውሮፕላን አብራሪው አደጋው ሲያጋጥም የጦር አውሮፕላኑ በእሳት ከመያያዙ በፊት አስቀድሞ በአየር መንሳፈፊያ ተንሳፎ ራሱን አድኗልም ተብሏል።
በአካባቢው ያለው የአሜሪካ አየር ሀይል አዛዥ ኮለኔል ፖል ታውንሰንድ እንዳሉት አደጋው ያጋጠመው አውሮፕላኑን ለማሳረፍ ጥረት እየተደረገ እያለ እንደሆነ ተናግረዋል።
ይህ አውሮፕላን 82 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ አለው የተባለ ሲሆን የአደጋው መንስኤ እየተመረመረ ነው ተብሏል።
በአሜሪካ የጦር አውሮፕላኖች ላይ መሰል አደጋ ሲፈጠር የአሁኑ የመጀመሪያው አይደለም የተባለ ሲሆን ባሳለፍነው ግንቦት ወር ተመሳሳይ የጦር አውሮፕላን ተከስክሷል።
ለዚህ የጦር አውሮፕላን መከስከስ ምክንያቱ አብራሪው የሰራው ስህተት እንደነበር በወቅቱ ተገልጿል።