የሱዳን ተቃዋሚዎች የቀድሞ አማጺዎችን ጭምር ያካተተ አዲስ ጥምረት መሰረቱ
በሚና ሚናዊ የሚመራው የሱዳን ነጻነት ንቅናቄ (SLM) እንዲሁም በጂብሪል ኢብራሂም የሚመራው የፍትህና እኩልነት ንቅናቄ (JEM) በጥምረቱ ተካተዋል
ጥምረቱ ትናንት ቅዳሜ ነው በካርቱም የተቃዋሚዎቹ አባላት በተገኙበት የተመሰረተው
የሱዳን ተቃዋሚዎች የቀድሞ አማጺዎችን ያካተተ አዲስ ጥምረት መሰረቱ፡፡
ጥምረቱ የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ኦማር ሃሰን አል በሽርን ከስልጣን ያስወገደውን አመጽ ከመራው የሲቪል ተቃዋሚዎች “የነጻነት እና ለውጥ ኃይሎች” ጥምረት የተለየ ነው ተብሏል፡፡
ጥምረቱ ትናንት ቅዳሜ ነው በካርቱም፤ “የነጻነት እና የለውጥ ኃይሎች አፈግፍገዋል” ባሉ የተቃዋሚ አባላት የተመሰረተው፡፡
ሱዳን በውስጥ ችግሯ “የውጭ ጣልቃገብነት”መፍቀድ የለባትም-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
ሱዳን ከአል በሽር ከስልጣን መወገድ በኋላ በዋናነት ከወታደራዊ ኃይሎች እና ከሲቪሊያን በተውጣጡ አካላት ነው እየተመራች ያለችው፡፡
ወደ ዲሞክራሲ ለመሻገር እንደሚበጅ በማሰብ በጊዜያዊነት የተቋቋመው ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት በሃገሪቱ ጦር መሪ በሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ነው የሚመራው፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ቢሆንም የሲቪሉ እና በወታደራ አመራሩ መካከል የሰፋ ልዩነት እንዳለ ይነገራል፡፡ በሽግግር ሂደቱ ላይ ጥላን እንዳያጠላም ነው የተሰጋው፡፡
ትናንት አዲሱን ጥምረት የመሰረቱትም “የነጻነት እና የለውጥ ኃይሎች” በሚጠበቀው እና ቃል በገቡት ልክ አይደሉም ያሉ ናቸው፡፡
ጥምረቱ የተለያዩ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጨምሮ በሚና ሚናዊ የሚመራውን የሱዳን ነጻነት ንቅናቄ (SLM)ን እንዲሁም በጂብሪል ኢብራሂም የሚመራውን የፍትህና እኩልነት ንቅናቄ (JEM)ን ያካተተ ነው፡፡
የአልበሽር ለአይ.ሲ.ሲ ተላልፎ መሰጠት ጉዳይ “በሱዳን ካቢኔ አባላት መካከል መከፋፈልን ፈጥሯል” ተባለ
በቅርቡ የዳርፉር ግዛት አስተዳዳሪ ሆኖ የተሾመው ሚናዊ “ጠንካራ የነጻነት እና የለውጥ ኃይልን ነው የምንፈልገው” ሲል በጥምረቱ ምስረታ መድረክ ላይ ተናግሯል፡፡
“የነጻነት እና የለውጥ ኃይል” ነን የሚሉ አካላት አዲስ ከተመሰረተው ጥምረት ጋር እንዲመካከሩም ጥሪ አቅርቧል፡፡
በጥምረቱ የምስረታ ስነ ስርዓት ላይ የሲቪል አስተዳደሩ መሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክም ሆኑ የሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት መሪው ሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን አልተገኙም፡፡
በቅርቡ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራን ያስተናገደችው ሱዳን በተለያዩ ተቃውሞዎች እየተናጠች ነው፡፡
ከሰሞኑ በምስራቃዊ ሱዳን የፍትሃዊ ውክልና እና ተጠቃሚነት ጥያቄን ባነሱ አካላት ወደቦች ጭምር የተዘጉበት ተቃውሞ ተቀስቅሶ እንደነበር ይታወሳል፡፡