የቤጃ ጎሳዎች ፖርት ሱዳንን መዝጋታቸውን ተከትሎ በካርቱም የነዳጅ እና የዳቦ እጥረት ማጋጠሙ ተገለጸ
አሜሪካ እና እንግሊዝ ለሱዳን የሲቪል አስተዳድር ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል
በሱዳን በወታደራዊ እና በሲቪል አመራሮች መካከል የተፈጠረው የፖለቲካ ውጥረት አሁንም እንደቀጠለ ነው
የቤጃ ጎሳዎች ፖርት ሱዳንን መዝጋታቸውን ተከትሎ በካርቱም የነዳጅ እና የዳቦ እጥረት ማጋጠሙ ተገለጸ።
የሱዳን ዋነኛ የገቢ እና ወጪ ንግዶች የሚከናወኑበት ፖርት ሱዳን የቤጃ ጎሳዎች ባስነሱት ተቃውሞ ከተዘጋ ከሶሰት ሳምንት በላይ ሆኖታል።
ከፖርት ሱዳን ወደ አገሪቱ ማዕከል ካርቱም እና ሌሎች ከተሞች የሚደረገው የትራንስፖርት እንቅስቃሴ አሁንም መስተጓጎሉ ተገልጿል።
ምስራቅ ሱዳን ተገቢውን ፖለቲካዊ ውክልና እና ጥቅም የማያገኝ ከሆነ ራሱን የቻለ ሀገር ይሆናል- የቤጃ ጎሳ መሪ
በዚህም ምክንያት በካርቱም የስንዴ ዱቄት እና ነዳጅ እጥረት ማጋጠሙን ሮይተርስ ዘግቧል።
እጥረቱ ወትሮም ቢሆን በሀይል እጥረት ውስጥ ላለችው ሱዳን ተጨማሪ ችግሮችን እየፈጠረ መሆኑን የገለጸው ዘገባው ችግሩን ለመፍታት በአገሪቱ መንግስት የተለያዩ እንቅስቃሴዎች በመደረግ ላይ ናቸው ብሏል።
የሱዳን ወታደራዊ እና ሲቪል አመራሮች እርስ በርሳቸው በመወቃቀስ ላይ ሲሆኑ የቤጃ ጎሳዎች ደግሞ በሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ተገቢው ውክልና አልተሰጠንም ከማለት ጀምሮ የተለያዩ ጉዳቶችን እያደረሰብን ነው ሲሉ ተቃውሟቸውን በማሰማት ላይ ናቸው።
የሱዳን የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ካሊድ ኦማር የሱፍ በበኩላቸው በሱዳን ያጋጠመውን የስንዴ ዱቄት እና የነዳጅ እጥረት ለመፍታት መንግስት ከመጠባበቂያ ክምችቶች በመውጣት እንደሚያከፋፍል ለሮይተርስ ተናግረዋል።
ሱዳን በውስጥ ችግሯ “የውጭ ጣልቃገብነት”መፍቀድ የለባትም-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
ባሳለፍነው አርብ አሜሪካ፤ እንግሊዝ እና ኖርዌይ የሱዳን የሲቪል አስተዳደር አመራሮች የፖለቲካ ውይይት በማድረግ በአገሪቱ የተፈጠሩ ውጥረቶችን እንዲያረግቡ አሳስቦ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።