ትራምፕ ከማህበራዊ ትስስር ገጾች የታገዱት ደጋፊዎቻቸውን በመቀስቀስ በካፒቶል ሂል ረብሻ አስነስተዋል በሚል ነበር
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ልጅ ኤሪክ ትራምፕ ሚስት በኢንስታግራም ገጿ የፕሬዘዳንቱን ድምጽ ለተከታዮቿ አጋርታ ነበር።
ከባለፈው ጥር ወር ጀምሮ በፌስቡክ ፤ትዊተር እና ዩቲዩብ የታገዱት ዶናልድ ትራምፕ ድምጻቸው እና ምስላቸው በሌላ ሰው በማህበራዊ ትስስር ገጾች ቢጋራም መታገዳቸው እንደቀጠለ ቢቢሲ ዘግቧል።
የዶናልድ ትራምፕ ልጅ ባለቤት የሆነችው ላራ ትራምፕ በኢንስታግራም ያጋራችው የዶናልድ ትራምፕ ምስል በፌስቡክ ኩባንያ መታገዱን የሚገልጽ ከፌስቡክ በኢሜሏ አማካኝነት የደረሳትን መልዕክት በስክሪን ሾት መልሳ አጋርታለች።
ኩባንያው እንዳስታወቀው ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ ሌሎች ከፌስቡክ እና ኢንስታግራም የታገዱ ሰዎችን ምስል እና ድምጽ ማጋራት ምስሎቹን ባጋራ ግለሰብ ላይም ተጨማሪ እገዳ ሊጣል እንደሚችል አስጠንቅቋል።
ዶኖልድ ትራምፕ ከማህበራዊ ትስስር ገጾች የታገዱት በጆ ባይደን በተሸነፉበት ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ሽንፈታቸውን አልቀበልም በማለት ለደጋፊዎቻቸው ያስተላለፉት መልዕክት በካፒቶል ሂል ለተፈጠረው ረብሻ ምክንያት ናቸው በሚል ነበር።