የፌስቡክ ኩባንያ አዲስ ስያሜ በያዝነው ወር መጨረሻ ላይ ይፋ ይደረጋል ተብሏል
የማሕበራዊ ትስስር ድረ ገጽ ኩባንያ ፌስቡክ በቅርቡ የስያሜ ለውጥ ሊያደርግ እንደሚችል ተገልጿል።
ዘ ቨርጅ የተሰኘው ድረገጽ እንደዘገበው ከሆነ ፌስቡክ በቀጣዮቹ ሳምንታት የኩባያውን የስያሜ ለውጥ ያደርጋል።
- ኢትዮጵያ ፌስቡክንና ትዊተርን በሀገራዊ የማህበራዊ ትስስር ገጽ የመተካት እቅድ እንዳላት አስታወቀች
- ፌስቡክ ኢትዮጵያን ዒላማ አድርገው መረጃ ሲያሰራጩ የነበሩ የግብፅ ገጾችን ዘጋ
ኩባንያው አገልግሎቱን በአዲስ መልክ ለማቅረብ ዝግጅት ማድረጉንም ነው ድረ ገጹ ያስታወቀው፡፡
በአዲሱ ስያሜ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ጥቅምት መጨረሻ ላይ ኩባንያው ዓመታዊ ጉባዔውን እንደሚያደርግ የተገለጸ ሲሆን፤ ዋና ስራ አስፈጻሚው ማርክ ዙከርበርግ ማብራሪያ ይሰጣል ተብሎም ይጠብቃል።
ኩባንያው አሁን ላይ ፌስቡክ፣ ዋትሳፕ፣ ኢንስታግራም እና ኦኩለስ የተሰኙ መተግበሪያዎችን አጠቃሎ ይዟል።
አዲስ ይፋ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው የኩባንያው ስያሜ እነዚህን መተግበሪያዎች ግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑም ተገልጿል።
በአዲስ መልክ በሚደራጀው ኩባንያ ሁሉም መተግበሪያዎች እንደሚተዳደሩ ይጠበቃል ሲል ድረ ገጹ ጽፏል።