የፌስቡክ መስራችና ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ፤ በሰዓታት ውስጥ 7 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ገንዘብ ማጣቱ ተገለጸ
ተቋርጠው የነበሩት አገልግሎቶቹ ስራ መጀመራቸውን ኩባንያው አስታውቋል
ዙከርበርግ ይህን ያህል ገንዘብ ያጣው የፌስቡክ፣ የኋትስ አፕ እና የኢንስታግራም አገልግሎቶች ለስድስት ሰዓታት ያህል ስራ ማቆማቸውን ተከትሎ ነው
የፌስቡክ መስራችና ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ ሰባት ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገቢ ማጣቱ ተገለጸ፡፡
ዙከርበርግ ይህን ያህል ገቢ ያጣው ራሱ መስርቶ የሚያስተዳድረው ኩባንያ ፌስቡክ አካ የሆኑ የፌስቡክ፣ የኋትስአፕ እና የኢንስታግራም አገልግሎቶች ለስድስት ሰዓታት ያህል ስራ ማቆማቸውን ተከትሎ ነው፡፡
በአገልግሎቱ መቋረጥ ምክንያት የፌስቡክ ኩባንያ የአክስዮን ድርሻ ማሽቆልቆሉ ተነግሯል፡፡ ከዓለም ቁንጮ ቱጃሮች ተርታ የተሰለፈው ዙከርበርግ በሃብት ደረጃው ዝቅ ማለቱም ነው የተነገረው፡፡
ኢትዮጵያ ፌስቡክንና ትዊተርን በሀገራዊ የማህበራዊ ትስስር ገጽ የመተካት እቅድ እንዳላት አስታወቀች
በብሉም በርግ የቢሊዬነሮች ዝርዝር ከማይክሮሶፍት መስራቹ ቢል ጌትስ አንድ ደረጃን ዝቅ ብሎ በ121 ነጥብ 6 ቢሊዬን ዶላር 5ኛ ደረጃ ላይ መቀመጡንም ነው ብሉምበርግ የዘገበው፡፡
እንደ ብሉምበርግ ከሆነ ዙከርበርግ በሳምንታት ውስጥ ነው ከነበረው 150 ቢሊዬን ዶላር ወደ 121 ነጥብ 6 ቢሊዬን ዶላር ዝቅ ያለው፡፡
ኔትብሎክስ የተሰኘው እንዲህ ዐይነት የአገልግሎት መቋረጦችንና ተጽዕኗቸውን ተከታታይ ኩባንያ የፌስቡክ እና የሌሎች መተግበሪያና አገልግሎቶቹ ተቋርጦ መቆየት ዓለምን 160 ሚሊዮን ዶላር አሳጥቷል ብሏል፡፡
በኢትዮጵያ ከሚፈጸመው የሳይበር ጥቃት 90 በመቶው በግንዛቤ ጉድለት የሚያጋጥም ነው
ፌስቡክ፣ ዋትስአፕ እና ኢንስታግራም በአለም ዙርያ ከአገልግሎት ውጪ መሆናቸውን ተራኪንግ ድረ ገጾች አስታውቀዋል።
በፌስቡክ ባለቤትነት የሚተዳደሩት ፌስቡክ፣ ዋትስ አፕ፣ ኢንስታግራም እና ሜሴንጀር እንዲሁም ሌሎች አገልግሎቶች ከትናንት አመሻሽ ጀምሮ ለ6 ያህል ሰዓታት ተቋርጠው ቆይተዋል፡፡
አገልግሎቶቹ አሁን ከሰዓታት መቋረጥ በኋላ መስራት የጀመሩ ሲሆን ለአገልግሎቶቹ መቋረጥ ይቅርታ የጠየቀው ኩባንያው ችግሩ የቴክኒክ ነው ብሏል።
ባጋጠመው ነገር ማዘኑን ገልጾ ይቅርታ የጠየቀው ማርክ ዙከርበርግም ወደ አገልግሎት መመለሳቸውን አስታውቋል፡፡
ስለ አገልግሎቱ መቋረጥ ባለሙያ የጠየቀው ዴይሊ ሜይል የኩባንያውን “ሰርቨሮች” ለማዘመን (አፕዴት) ለማድረግ በሚሞከርበት ሰዓት ያጋጠመ እክል ሳይሆን እንዳልቀረ ዘግቧል፡፡