በመንግስት ግልበጣ የመጣው የቡርኪናፋሶ ጁንታ የተቃጣበትን መፈንቅለ መንግስት ማክሸፉን ገለጸ
የጸጥታና ደህንነት መኮንኖች ሀገሪቱን ለመበታተን አሲረዋል ብሏል
የመፈንቅለ መንግስት አቀነባባሪዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው ተብሏል
በመንግስት ግልበጣ የመጣው የቡርኪናፋሶ ጁንታ የተቃጣበትን መፈንቅለ መንግስት ማክሸፉን ገለጸ።
የቡርኪናፋሶ ወታደራዊ ጁንታ በጸጥታና በደህንነት ኃይሎች የተደረገበትን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ማክሸፉን አስታውቋል።
ራሱ መንግስት ገልብጦ ስልጣን የያዘው ወታደራዊ መንግስት ባወጣው መግለጫ መኮንኖችና ሌሎች ሰዎች ሀገሪቱን ለመበታተን አሲረዋል ብሏል።
መንግስት ሙከራውን "የሪፐብሊኩን ተቋማት ለማጥቃት እና ሀገራችንን ወደ ትርምስ የመክተት ጨለማ ዓላማ"ሲል ገልጾታል።
የመፈንቅለ መንግስት ሞካሪዎችን በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑን በስም ሳይጠቅስ አስታውቋል።
የወታደራዊ መንግስቱ አቃቢ ህግ አራት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጠቅሶ፤ ሁለት ሰዎች ደግሞ ማምለጣቸውን ተናግሯል።
ጁንታው "ምርመራ የሴራውን አነሳሾችን ለማወቅ ይረዳል" ብሏልም።
ጁንታው መንግስት ሰኞ ዕለት በቡርኪናፋሶ ታጣቂ ኃይሎች ውስጥ ያለውን ውጥረት የዘገበውን የፈረንሳይ ጄን አፍሪኬን መጽሄት "ከእውነት የራቀ" ጽሁፍ በማሳተሙ አግዶታል።
በማግስቱ በሽህዎች የሚቆጠሩ የጁንታው ደጋፊዎች በዋና ከተማይቱ ኦጉዱጉ ጎዳናዎች እና በሌሎችም ስፍራዎች በባለስልጣናቱ ላይ ልዩነት አለ መባሉን በማስተባበል ሰልፍ ወጥተዋል።
የቡርኪናፋሶ ጁንታ ወደ ስልጣን የመጣው ባለፈው ዓመት ሁለት ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ካደረገ በኋላ ነበር።
ከአልቃይዳ እና እስላማዊ መንግስት ጋር ግንኙነት ባላቸው ታጣቂ ቡድኖች የተባባሰው ጥቃት ለመንግስት ግልበጣው መንስኤ መሆኑ ይነገራል።