ለ20 ዓመታት ያለ ምንም ትምህርት የቀዶ ጥገና ህክምና ሲሰጥ የቆየው ሀሰተኛ ሐኪም
ግለሰቡ ትምህርቱን ከዘጠነኛ ክፍል ያቋረጠ ነበር ተብሏል
ለዓመታት ህክምና ሲሰጥ የቆየው ይህ ሀሰተኛ ሐኪም የብልት መጠን መጨመር የቀዶ ጥገና ህክምና ሲሰጥ እንደነበር ተገልጿል
ለ20 ዓመታት ያለ ምንም ትምህርት የቀዶ ጥገና ህክምና ሲሰጥ የቆየው ሀሰተኛ ሐኪም ታሰረ፡፡
የ36 አመቱ ታይላንዳዊ ላለፉት 20 ዓመታት ለበርካታ ህክምና ፈላጊዎች የቀዶ ህክምና ሲሰጥ ቆይቷል፡፡
በአንድ ወር ውስጥ በአማካኝ ለሁለት ታካሚዎች አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበር የሚነገረው ይህ ታይላንዳዊ ከሰሞኑ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
ኪቲኮርን ሶንግስሪ የሚባለው ይህ ሰው በማዕከላዊ ታንላንድ በምትገኘው ሳሙት ሳኮን በተሰኘችው ከተማ ይኖር ነበር፡፡
ይህ ግለሰብ በዚች ከተማ በብልት ቀዶ ጥገና ህክምና ታዋቂነትን ያተረፈ ሲሆን አንድ ደንበኛው ባቀረበበት ክስ ምክንያት ባሳለፍነው ሳምንት ለእስር መዳረጉን ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡
የብልት መጠን መጨመር ቀዶ ህክምና የተዋጣልኝ ሐኪም መሆኑን የሚናገረው ይህ ሰው በፖሊስ ከታሰረ በኋላ ሀሰተኛ ሐኪም መሆኑን ተናግሯል፡፡
ሕክምና የትም አልተማርኩም፣ ነገር ግን ገና ከ14 ዓመቴ ጀምሮ ራሴን በልምድ አስተምሬያለሁ የሚለው ይህ ሰው የህክምና ፈቃድም ሆነ ከየትኛውም የህክምና ተቋም የተማረበትን ማስረጃ ማቅረብ አልቻለም፡፡
በግርዛት ምክንያት የተጎዳን የሴት ብልት አካል ማስመለስ እንደሚቻል ያውቃሉ?
ይህን ተከትሎም ላለፉት 20 ዓመታት ፈቃድ አለኝ በሚላት የግል ክሊኒክ ውስጥ አንድ ደንበኛን እስከ 7 ሺህ ባህት ወይም 150 ዶላር ክፍያ ሲያስከፍል እንደነበር ተናግሯል፡፡
ግለሰቡ አክሎም እስካሁን ቀዶ ጥገና ህክምና ካደረኩላቸው ተገልጋዮቼ ውስጥ ቅሬታ ያቀረበ አልነበረም ያለ ሲሆን በቅርቡ ህክምና ያደረገለት አንድ ደንበኛው ግን ህክምናው አልሰራልኝም እንዳለው ለፖሊስ ተናግሯል ተብሏል፡፡
ለፖሊስ ጥቆማ የሰጠው እና የህክና ካሳ ይከፈለኝ በሚል ክስ ያቀረበው አንድ ተገልጋይ በበኩሉ የብልቱ መጠን እንዲጨምርለት በሚል ወደ ክሊኒኩ እንደሄደ እና ከህክምናው በኋላ ብልቱ በግንኙነት ወቅት ሊቆምለት እንዳልቻለ ለፖሊስ ተናግሯል፡፡