የማራዶና ቤተሰቦች የቀድሞውን እግር ኳስ ኮከብ አፅም ወደ ሌላ ቦታ ለማዘወር ጠየቁ
ማራዶና በ2020 ነበር በተወለደ በ60 አመቱ በልብ ህመም ምክንያት ህይወቱ ያለፈው
የናፖሊ ደጋፊዎች እና የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ማራዶናን "የእግር ኳስ ፈጣሪ" በማለት እስከማምለክ ደርሰዋል
የማራዶና ቤተሰቦች የቀድሞውን እግር ኳስ ኮከብ አፅም ወደ ሌላ ቦታ ለማዘወር ጠየቁ
የማራዶና ልጆች የቀድሞውን ታላቅ የእግር ኳስ ኮከብ ዲያጎ ማራዶናን አፅም ደህንነቱ ወደተጠበቀ እና ህልፈቱን ለሚዘክሩ ደጋፊዎች ወደሚመች የቤተሰብ የመቃብር ህንጻ ወይም ማውዞሊየም እንዲዛወር የአርጀንቲና ባለስልጣናትን ጠይቀዋል።
ከአራት አመታት በፊት ህይወቱ ያለፈው ማራዶና ስርአተ ቀብሩ የተፈጸመው ከቡነስ አየርስ ወጣ ብሎ በሚገኝ የግል መካነ መቃብር ነው።
በዚህ ቦታ ቤተሰቦች ብቻ ናቸው እንዲገቡ የሚፈቀድላቸው።
'ሚሞሪያል ዴል ዳይዝ' የተባለው የቤተሰብ የመቃብር ህንጻ ከአርጀንቲና መንግስት ስራ አስፈፃሚ ቅርንጫፍ ጀርባ እንደሚገኝ እና ለህዝብ ክፍት እንደሚሆን የማራዶና ትንሹ ልጅ እናት ቬሮኒካ ኦጀዳ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኻን መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
የማራዶና ልጆች ዳልማ፣ ጂያኒና እና ኦጀዳ ማራዶናን በመወከል ለፍርድ ቤት ያቀረቡት ማስታወሻ "ሁሉም ወራሾች በጋራ ስምምነት ወደ ቀጣይ ማረፊያው እንዲዛወር በጋራ ስምምነት ባለስልጣናትን ጠይቀዋል...አሁን ካለበት የተሻለ ደህንነት ወደአለበት ቦታ" ይላል።
በማራዶና ሞት፤ የግል ሐኪሞቹን ጨምሮ 8 የህክምና ባለሙያዎች ሊከሰሱ ነው
የማራዶና ልጆች፣ ሁሉም አርጀንቲናውያን እና የአለም ህዝብ በእግር ኳስ ታሪክ አንጸባራቂ የሆነውን ማራዶናን መዘከር የሚችሉበት ሁኔታ ይመቻቻል ብለዋል።
ከቤተሰቦቹ ጠበቃ አንደኛው እንደገለጹት የአፅም ማዛወሩ ተግባር የሚካሄደው የ1986ቱ የዓለም ዋንጫ አሸናፊ ማራዶና በተወለደበት በፈረንጆች ጥቅምት 30 ነው።
ማራዶና በ2020 ነበር በተወለደ በ60 አመቱ በልብ ህመም ምክንያት ህይወቱ ያለፈው። የናፖሊ ደጋፊዎች እና የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ማራዶናን "የእግር ኳስ ፈጣሪ" በማለት እስከማምለክ ደርሰዋል።