የአለም ድንቃድንቅ መዝገብም አስገራሚው ግጥምጥሞሽ ክብረወሰን ሰብሯል በሚል መዝግቦታል
በፓኪስታኗ ላካርና ከተማ ነዋሪ የሆነው አሚር አሊ ባለቤቱን ከድጃ ያገባው በልደቱ ቀን ነው።
የትዳር አጋሩ ከድጃም በተመሳሳይ በልደቷ ቀን ነው ከአሚር ጋር በትዳር የተሳሰረችው።
በተወለዱበት ቀን የተጋቡት ጥንዶች የወለዷቸው ሰባት ልጆችም የልደት ቀናቸውን የሚጋሯቸው ሆነዋል።
ዘጠኙም የቤተሰቡ አባላት ነሃሴ 1 እንደመወለዳቸው በተለያየ ቀን የልደት ድግስ አይኖራቸውም፤ ልደታቸውን በጋራ አድምቀው ያከብሩታል።
- በልደታቸውን ቀን የመጀመሪያ ልጃቸውን ያገኙት አሜሪካውያን ጥንዶች
- ያለፍላጎቱ የልደት በዓሉን ያከበረለትን ድርጅት የከሰሰ አንድ ሰራተኛ 450 ሺህ ዶላር ካሳ ተከፈለው
በፈረንጆቹ 1991 (በልደታቸው ቀን) የተጋቡት አሚር እና ከድጃ አንደኛ አመት የጋብቻ በዓላቸውን በሚያከብሩበት እለት የመጀመሪያዋን ሴት ልጃቸውን አግኝተዋል።
ተከታትለው የመጡት በ1998 እና 2003 የወለዷቸው የሴት እና ወንድ መንትያ ልጆቻቸውም ሆነ ቀሪዎቹ ሁለት ልጆች ነሃሴ 1 ነው የተወለዱት።
ከድጃ ሁሉንም ልጆቿን አምጣ መውለዷንና ተፈጥሮ ከፈቀደችው ያልጊዜው ፈጥኖ የተወለድ ልጅ እንደሌላቸው የሚጠቅሰው አሚር፥ ሆን ብለው የልጆቹን የልደት ቀን ተመሳሳይ እንዲሆን እንዳላደረጉ ይናገራል።
“የፈጣሪ ስጦታ እንጂ ሂሳብ ሰርተን ያመጣነው ጉዳይ አይደለም” ሲልም ነው የገለጸው።
የአለም ድንቃድንቅ መዝገብ የእነአሜርን ቤተሰብ ተመሳሳይ የልደት ቀን የሚጋራ በርካታ ቤተሰብ በሚል መዝግቧል።
ከዚህ ቀደም በአሜሪካ የኩሚንስ ቤተሰብ አምስት ልጆች በተመሳሳይ ቀን በመውለድ ሪከርዱን ይዘው መቆየታቸው ለትውስታ ተነስቷል።