የሰሜን ኮሪያው መሪ የሀገሪቱን የቀን መቁጠሪያ በአያታቸው የልደት ቀን ተኩ
በሰሜን ኮሪያ የግሪጎሪያን ካላንደርን መጠቀም በማቆም፤ 2022 ዓመትንም ሰርዛለች
ከ1912 የሚጀምረው አዲሱ ቀን መቁጠሪያ፤ ዘንድሮ “ጁች 111” በሚል ይጠራል
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሀገሪቱ ስትጠቀምበት የቆየውን የግሪጎሪያን የቀን መቁጠሪያ (ካላንድር) በአያታቸው የልደት ቀን እንዲተካ መወሰናቸው ተሰምቷል።
በዚህም መሰረት ሀገሪቱ የግሪጎሪያን አቆጣጠርን ከቀን አቆጣጠር ስርዓቷ ያወጣች ሲሆን፤ አሁን ያለንበትን የፈረንጆቹን 2022 ዓመትንም ሰርዛለች።
ይህንን ተከትሎም የሰሜን ኮሪያ የዜና ኤጀንሲ የግሪጎሪያን የቀን አቆጣጠርን በመተው በሰሜን ኮሪያው መሪ አያት ልደት ቀን የሚጀምረውን የቀን አቆጣጠር መጠቀም ጀምረዋል።
የዜና ኤጀንሲው ከዚህ ሳምንተ ጀምሮም በ2022 ምትክ “ጁች 111” የሚል የቀን አቆጣጠር መጠቀም መጀመራቸውም ነው የተነገረው።
“ጁች” የሚለው ቃል የሰሜን ኮሪያ መስራች እንደሆኑ የሚነገርላቸው የአሁኑ የሀገሪ መሪ አያት ኪም ኢል ሱንግ አብዝተው ከሚጠቀሙት ቃል የተወሰደ ሲሆን፤ ትርጉሙም “ራስን የመቻል መንፈስ” የሚል ነው ተብሏል።
አዲሱ የሰሜን ኮሪያ “ጁች” የዘመን መቁጠሪያ የሰሜን ኮሪያ የመጀመሪያ መሪ በሆኑት ኪም ኢል ሱንግ የልደት ቀን የሚጀመር ሲሆን፤ የዘመን መቁጠሪያው የመጀመሪያ ዓመትም የፈረንጆቹ 1912 ነው ተብሏል።
የዘመን መቁጠሪያው የሰሜን ኮሪያ የመጀመሪያ መሪ በሆኑት ኪም ኢል ሱንግ ከዚህ ዓለም በሞት በተለዩበት በፈረንጆቹ 1997 ላይ እንደተዋወቀ ይነገርለታል።
ሆኖም ግን የሀገሪቱ የዜና ኤጀንሲ እስካሳለፍነው ሳምንት ድረስ የግሪጎሪያውያን የቀን መቁጠሪያን ሲጠቀሙ ቆይተዋል።
አሁን ላይ የቀን መቁጠሪያውን መጠቀም የተጀመረው ከሳምንታት በኋላ በደማቅ ሁኔታ የሚከበረውን ኪም ኢል ሱንግ 110ኛ የልደት በዓል ምምንያት በማድረግ ነው ተብሏል።
ሰሜን ኮሪያ ከዚህ ቀደምም ተመሳሳይ እርምጃዎችን ስትጠቀም መቆየቷ የሚታወስ ሲሆን፤ በፈረንጆቹ 2015 ላይ የራሷ የሆነ የየፒዮንግያነግ ሰዓት አቆጣጠር” ይፋ ማድረጓ ይታወሳል።
በዚህም ሰሜን ኮሪያ ከዚህ ደቀም ከደቡብ ኮሪያ ጋር ትጠቀም የነበረውን ተመሳሰይ ሰዓት በ30 ደቂቃ እንዲቀድም አድርጋ ነበር።