ቪንሺየስ ጁኒየር የጥላቻ ምልክት ያሳየውን ደጋፊ በፍጥነት ያስወጣውን ሲቪያን አደነቀ
ቪንሺየስ የዝንጀሮ ምልክት(ጀስቸር) የሚያሳይን ሰው ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ አጋርቷል
ቪንሺየስ ይህ የዘረኝነት ጥቃቅ የደረሰበት ሪያል ማድሪድ እና ሲልቫ 1-1 አቻ በወጡበት ጨዋታ ነው
ብራዚላዊው የሪያል ማድሪድ ኮከብ የጥላቻ ምልክት ያሳየውን ደጋፊ በፍጥነት ያስወጣውን ሲቪያን አድንቋል።
ቪንሺየስ ይህ የዘረኝነት ጥቃት የደረሰበት ሪያል ማድሪድ እና ሲልቫ 1-1 አቻ በወጡበት ጨዋታ ነው።
ቪንሺየስ የዝንጀሮ ምልክት(ጀስቸር) የሚያሳይን ሰው ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ አጋርቷል።
ይህ ጥቃት "19ኛው ክፍል ነው፤ ይቀጥላል" ያለው ቪንሺየስ የስፔን ባለስለጣን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ህጉን እንዲያሻሽሉት ጥሪውን አቅርቧል።
ለስፔን እግርኳስ አሳዛኝ በሆነው ክስተት ሲቪያ በፍጥነት እርምጃ መውዱን የ23 አመቱ ቪንሺየስ አድንቋል።
ቪንሺየስ ጨምሮም "እንዳለመታደል ሆኖ በቅዳሜ ጨዋታ ሌላም ዘረኛ ቪዲዮ ተመልክቻለሁ። ይህ የተካሄደው ደግሞ በህጻን ነው። የሚያስተምራቸው ባለመኖሩ አዝናለሁ።" ብሏል።
ሲቪያ "ዘረኛ እና መጤ ጠል የሆነ ንግግር መኖሩን ባወቅን ጊዜ እንዲለይ እና ከስቴድየም ወጥቶ ለህግ አካል እንዲሰጥ" ማድረጉን ገልጿል።
ሲልቫ ኤፍሲ በግለሰቡ ላይ እርምጃ መወሰዱን እከታተላለሁ ብሏል።
ባለፈው ግንቦት ወር ሪያል ማድሪድ ከቫሌንሺያ ጋር በነበረው ጨዋታ ቪንሺየስ የጥላቻ ንግግር ሰለባ ሆኖ ነበር።
የቪንሺየስ ክለብ ሪያል ማድሪድም ለስፔን አቃቤ ህግ ቅሬታ ማቅረቡ ይታወሳል።
"እነዘህ ሰዎች በወንጀል መቀጣት አለባቸው" ያለው ቪንሺየስ ህግን ማሻሻል የ2030 ዓለም ዋንጫን ለምታዘጋጀው ስፔን ወሳን እርምጃ ነው ብሏል።