ቪንሺየስ ጁኒየር የሪያል ማድሪድ ቆይታውን ለማራዘም ኮንትራት ፈረመ
የ23 አመቱ ተጨዋች በ48 ሚሊዮን ዶላር የዝውውር ዋጋ ነበር በ2018 ከፍላሚንጎ ሪያል ማድሪድን የተቀላቀለው።
ቪንሺየስ ክለቡን ከተቀላቀለ በኋላ 235 ጨዋታዎችን አድርጎ 62 ግቦችን አስቆጥሯል
ቪንሺየስ ጁኒየር የሪያል ማድሪድ ቆይታውን ለማራዘም ኮንትራት ፈረመ።
ብራዚላዊው የክንፍ ተጨዋች ቪንሺየስ ጁኒየር በሪያል ማድሪድ ያለውን ቆይታ አራዝሟል።
ሪያል ማድሪድ በትናንትናው እለት እንዳስታወቀው የክንፍ ተጨዋች የሆነው ቪንሺየስ ከሪያል ማድሪድ ጋር እስከ 2027 ድረስ የሚያቆየውን ኮንትራት ፈርሟል።
የ23 አመቱ ተጨዋች በ48 ሚሊዮን ዶላር የዝውውር ዋጋ ነበር በ2018 ከፍላሚንጎ ሪያል ማድሪድን የተቀላቀለው።
ቪንሺየስ ክለቡን ከተቀላቀለ በኋላ 235 ጨዋታዎችን አድርጎ 62 ግቦችን አስቆጥሯል።
"ሪያል ማድሪድ ክለብ እና ቪንሺየስ ጁኒየር ስምምነት ላይ ደርሰዋል፤ ስምምነቱ ቪንሺየስን እስከ ሰኔ 30፣ 2027 ያቆየዋል" ብሏል ሪያል ማድሪድ ባወጣው መግለጫ።
ሰኞ እለት በተካሄደው የባለንዶር ሽልማት ባለው የሰብአዊነት ተሳትፎ የሶቅራጥስ ሽልማት ያሸነፈው ሺንሺየስ ከሪያል ማድሪድ ጋር ዘጠኝ ሽልማቶችን አሸንፏል።
ቪንቪየስ በስፔን ቆይታው ተደጋጋሚ የሆነ የዘረኝነት ጥቃትን አስተናግዷል።
ሪያል ማድሪድ ከሲልቪያ ጋር ባደረገው ጭዋታ ከሲልቪያ ደጋፊ የደረሰበት የዘረኝነት ጠቃት የቅርብ ጊዜው ነው።
ቪንሺየስ የስፔን ባለስልጣናት እነዚህ አጥፊዎች የሚቀጡበትን ህግ ሊያወጡ ይገባል ሲል ቅሬታውን ማቅረቡ ይታወሳል።