በደቡብ ኮሪያ ውሻን በተመለከተ የወጣው ህግ ፖሊስ እና አርሶ አደሮችን አጋጨ
በኮሪያ ባለፈው አመት በተሰራ የዳሰሳ ጥናት 2/3 የሚሆኑት ኮሪያውያን የውሻ ስጋ መብላትን ይቃወማሉ
መንግስት በውሻ እርባታ እና መሸጥ የተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች ስራ በሚያቆሙበት ጊዜ እንዳይጎዱ የፋይናንስ ድጋፍ እንደሚያደርግም ቃል ገብቷል
የደቡብ ኮሪያ አርሶአደሮች መንግስት የውሻ ስጋ እንዳይበላ ለማገድ የሚያስችል ረቂቅ ህግ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል።
ውሻን ለምግብነት ሲያረቡ እና ሲያሳድጉ የነበሩ 200 ገደማ የደቡብ ኮሪያ አርሶአደሮች መንግስት የውሻ ስጋ እንዳይበላ ለማድረግ ያወጣውን እቅድ እንዲሰርዝ በፕሬዝደንቱ ጽ/ቤት አቅራቢያ ሰልፍ ማካሄዳቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ውሾችን በካርጎ ጭነው በፕሬዝደንቱ ጽ/ቤት በኩል ባለው መንገድ ለማለፍ እና ለመልቀቅ የሞከሩ በደርዘን የሚቆጠሩ አርሶ አደሮች ፖሊስ ፍተሻ በማድረጉ እንዲመለሱ መደረጋቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
የገዥው ፖርቲ ፕሬዝደንት ዩን ሱክ ዮል በሀገሪቱ ውሻን ለምግብነት ማርባት እና መሸጥን የሚከለክል ህግ ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።
መንግስት በውሻ እርባታ እና መሸጥ የተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች ስራ በሚያቆሙበት ጊዜ እንዳይጎዱ የፋይናንስ ድጋፍ እንደሚያደርግም ቃል ገብቷል።
በውሻ ስጋ መብላት ዙሪያ ያለውን ውዝግብ መቋጫው አሁን ነው ያሉት የፖርቲው አባላት ፖርላማውን ከተቆጣጠረው የተቃዋሚ ፖርቲም ሰፊ ድጋፍ ማግኘታቸውን ገልጸዋል።
51 ሚሊዮን ህዝብ ባላት ደቡብ ኮሪያ ውስጥ ከስድስት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ቤተሰቦች ለማዳ የቤት ውሻ አላቸው ተብሏል።
በኮሪያ ባለፈው አመት በተሰራ የዳሰሳ ጥናት 2/3 የሚሆኑት ኮሪያውያን የውሻ ስጋ መብላትን ይቃወማሉ፣ ይህም ከ2015 በ27 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል።
ተቃውሞውን የመራው የኢንዱስትሪ ተወካይ ጁ ዮንግ ቦንግ ፖለቲከኞች እንዲስትሪዎችን የመዝጋት ወይም ሰዎች ምን መብላት እንዳለባቸው የመምረጥ መብት የለቸውም ብሏል።
ጁ "ውሻ መብላት ኃላቀር ነው በሚለው ሀሳብ አንስማማም። ምክንያቱም እንስሳትን ማራባት የጀመሩ ሁሉም ሀገራት የሆነ ወቅት ውሻ ይበሉ ነበር፤ አሀንም የሚበሉ አሉ።" ብሏል
ጁ አርሶ አደሮች በረቂቅ ህጉ ላይ እንዳይወያዩ መደረጋቸውን እና ይሰጣቸዋል የተባለው የፋይንስ ድጋፍም በቂ አለመሆኑን ገልጿል።
በሰልፉ አርሶ አደሮቹ እንቅስቃሴያቸውን ሊያስቆም ከመጣው ከፍተኛ ቁጥር ካለው ፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል።
ከሰልፉ በኋላ ጁን ጨምሮ ሶስት ሰዎች መታሰራቸውን የሰልፉ አስተባባሪዎች ተናግረዋል።