ካራች በተሰኝችው ከተማ በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች መበራከት የብዙ ወላጆች ስጋት ነው
ቤተሰብ የልጁን ደህንነት ለመከታተል የተለያዩ ነገሮችን ሲያደርግ መመልከት የወላጅ ደምቡ ነው፡፡
ወላጆች ልጆቻቸው ከቤት ውጪ የሚኖራቸውን እንቅስቀሴ ሰላማዊ መሆኑን ለማረጋገጥ አቅማቸው ከፍ ያለ እና ገንዘብ ያላቸው ሰዎች የግል ጥበቃ ሲቀጥሩ ሌሎች ደግሞ የልጆችን እንቅስቀሴ በመገደብ ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ መጣራቸው አዲስ ነገር አይደለም፡፡
ከወደ ፓኪስታን የሰማው ዜና ግን እስካሁን ከታዩት የጥብቃ አይነቶች ለየት ያለ ይመስላል፡፡
የልጁን ደህንነት ለመቆጣጠር በጭንቅላቷ ላይ የደህንት ካሜራ ያስገጠመው አባት ከሰሞኑ መነጋገርያ ሆኗል፡፡
ፓኪስታናዊው አባት በተለምዶ በመኖርያ ቤቶች እና በድርጅቶች ላይ የሚገጠመውን መጠኑ ከፍ ያለ የደህንነት ካሜራ በጭንቅላቷ ላይ አድርጋ እንድትንቀሳቀስ ወስኗል፡፡
አባት ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ካራቺ በተባለው ከተማ አንዲት ሴት ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ተገድላ መገኝቷን ተከትሎ ነው፡፡
ልጁ ከቤት ውጭ በሚኖራት ውሎ ሁሌም ስጋት እንደሚገባው የሚናገረው አባት በካሜራው አማካኝነት ውሎዋን እና እንቅስቃሴዋን መቆጣጠር በመቻሉ ጥቂትም ቢሆን እፎይታ እንደተሰማው ተናግሯል፡፡
ወጣቷ ሴት ከጋዜጠኞች ጋር ባደረገችው ቃለ መጠይቅ ካሜራውን ተሸክማ መዋሏ የቤተሰቦቿን እለታዊ ጭንቀት በማስቀረት ስለ ደህንነቷ እርግጠኛነት እንዲሰማቸው ሰለሚያደርግ በካሜራው ቅር እንደማትሰኝ ተናግራለች፡፡
በተጨማሪም ካራቺ በተባለው ወጣቷ በምትኖርባት ከተማ በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት አስጊነት ደረጃ ከፍተኛ መሆኑን ተከትሎ ወላጆች መሰል ለሰዎች ግራ የሚያጋቡ ውሳኔዎችን ቢሰውኑ አያስገርሙም ነው ያለችው፡፡
ጉዳዩ በማህበራዊ ትስስር ገጽ መነጋገርያ መሆኑን ተከትሎ ብዙዎች የወላጆችን የስጋት ደረጃ መረዳት ቢችሉም ካሜራው ምን ያህል የደህንት ዋስትና ሊሆን እንደሚችል ግን ጥያቄ አንስተዋል፡፡
ሌሎች ደግሞ ካሜራው የልጅቷን ማህበራዊ መደበኛ ህይወት የሚጋፋ ነጻነቷንም የሚጥስ ነው ሲሉ ድርጊቱን ተቃውመውታል፡፡