“ፊቼ ጫምባላላ” አከባበር በምስል
የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል “ፊቼ ጫምባላላ” ዛሬ ተከብሯል
በዓሉ 'ቄጣላ' ብህረ ዝማሬና በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች ታጅቦ ተከብሯል
ሲዳማ የዘመን መለወጫ የሆነው “ፊቼ ጫምባላላ” በዓል በሀዋሳ ከተማ የፍቅር ሀይቅ ዳርቻ በሚገኘው 'ሶሬሳ ጉዱማሌ' በዛሬው እለት ተከብሯል።
''ፊቼ ጨምበላላ'' በዓል አብሮነት፣ ሰላም፣ መረዳዳትን በሚያጠናክሩ ክንውኖች ታጅቦ ነው ዛሬ የተከበረው።
ሲዳማ የዘመን መለወጫ የሆነው “ፊቼ ጫምባላላ” በዓል 'ቄጣላ' ህብረ ዜማ እና በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች ታጅቦ በደማቅ ስነ ስርዓቶች ተከብሯል።
በዓሉ ላይ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች ታድመዋል።
የሲዳማ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ ወሰንየለህ ሰምኦን፣ በዓሉ ወደ አዲሱ ዓመት የመሸጋገሪያ ብስራት ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።