በግምገማ ጊዜው ውስጥ አንጸባራቂ ብቃት ያሳዩ ተጨዋቾች እና አሰልጣኞች ቁጥር በሁሉም ዘርፍ ወደ ሶስት ምርጥ እጩ ዝቅ ብሏል
የፊፋ "ምርጥ" ሽልማት ዛሬ ምሽት ይካሄዳል።
ከመላው አለም የተመረጡ ኮኮቦች በተለያዩ ዘርፍ ሽልማት ይዘው ወደ ሀገራቸው የሚመለሱበት "ዘ ቤስት ፊፋ አዋርድስ 2023" ዛሬ ምሽት ይካሄዳል።
በሽልማቱ ይፋዊ ዌብሳይት መሰረት የፊፋ ምርጥ ሽልማት በዘጠኝ ዘርፎች ይካሄዳል።
በግምገማ ጊዜው ውስጥ አንጸባራቂ ብቃት ያሳዩ ተጨዋቾች እና አሰልጣኞች ቁጥር በሁሉም ዘርፍ ወደ ሶስት ምርጥ እጩ ዝቅ ብሏል።
11 የወንጆች እና የሴቶች ብሔራዊ ቡድኖች የተመረጡ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ሶስቱ ለፊፋ ፋን ምርጥ ሽልማት ታጭተዋል።
የፊፋ ፌር ፕሌይ አዋርድ ሌላኛው ሽልማት ነው።
ፊፋ ሽልማት ከጀመረበት ከፈረንጆቹ 2016 ጀምሮ በዚህ ዘርፍ የሚሰጠው ሽልማት ስምንተኛ እንደሚሆን ዌብ ሳይቱ ጠቅሷል።
በዚህ ዘርፍ ሊዮነል ሜሲ፣ ማኑየል ኑየር እና ሜጋን ራፓኖ ይህን ሽልማት ማንሳት ችለዋል።
የሴቶች የምርጥ ተጨዋች ግምገማ ( ምርጥ ተጨዋች፣ የሴቶች የአመቱ አሰልጣኝ እና ምርጥ ግብ ጠባቂ) የተካሄደው ከፈረንጆቹ ነሐሴ 1፣2022 የሴቶች የአለም ዋንጫ ፍጻሜ እስከተካሄደበት ነሐሴ 20፣2023 ባለው ጊዜ ውስጥ ነው።
ከፈረንጆቹ ታህሳስ 20፣2022 እስከ ነሐሴ 20፣2023 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ደግም ምርጥ የወንድ ተጨዋቾች ልየታ ተካሂዷል።
የፊፋ ምርጥ ሽልማቶች፦
ሽልማቶቹ በዘጠኝ ዘርፎች የተከፋፈሉ ናቸው።
- የፊፋ ምርጥ የወንድ ተጨዋች ሽልማት
- የፊፋ ምርጥ የሴት ተጨዋች ሽልማት
-የፊፋ ምርጥ ግብ ጠባቂ ሽልማት
-የፊፋ ምርጥ የሴት ግብ ጠባቂ ሽልማት
-የፊፋ ምርጥ የወንድ አስልጣኝ ሽልማት
-የፊፋ ምርጥ የሴት አሰልጣኝ ሽልማት
-የፋፊ ፑስካስ ሽልማት ለምርጥ ግብ የሚሰጥ
-የፊፋ ፌየር ፕሌይ ሽልማት
-የፊፋ የደጋፋ ሽልማት
-የፊፋ ምርጥ ቡድን ሽልማት