የቀድሞው የፊፋ ፕሬዝደንት ብላተር ዓለም ዋንጫን በተመለከተ የተላለፈውን ውሳኔ አጣጣሉ
ብላተር በ2030፣ 100አመት የሚሞላው የዓለም ዋንጫ የመጀመሪያውን ውድድር ባዘጋደችው እና ባነሳችው ኡራጓይ መካሄድ አለበት ብለዋል
የቀድሞው የፊፋ ፕሬዝደንት ሴፕ ብላተር የዓለም ዋንጫ በሶስት አህጉር ውስጥ ባሉ ስድስት ሀገራት እንዲካሄድ የተላለፈውን ውሳኔ አጣጥለዋል
የቀድሞው የፊፋ ፕሬዝደንት ሴፕ ብላተር የዓለም ዋንጫ በሶስት አህጉር ውስጥ ባሉ ስድስት ሀገራት እንዲካሄድ የተላለፈውን ውሳኔ አጣጥለዋል።
ፊፋ ባለፈው ሮብዕ እለት እንዳስታወቀው የ2030 የዓለም ዋንጫን ለየት ለማድረግ ሞሮኮ፣ ስፔን እና ፖርቹጋል ውድድሩን አንዲያዘጋጁ እንዲሁም ኡራጓይ፣ አርጀንቲናና እና ፖራጓይ ደግሞ መክፈቻ ጨዋታዎችን እንዲያስተናግዱ ወስኗል።
ፊፋን ከፈረንጆቹ 1998-2015 የመሩት እና በሙሰና ክስ ምክንያት ስልጣን የለቀቁት ሴፕ ብላተር ይህን ውሳኔ መተቸታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
"ውድድሩን በዚህ መልኩ ማራራቅ ደስ አይልም" ሲሉ ብላተር ለስዊድን ጋዜጣ ተናግረዋል።
የአለም ዋንጫ አንድ ቦታ የሚካሄድ ክስተት መሆን አለበት ያሉት ብላተር ይህ ለውደድሩ፣ለተጨዋቾቹ፣ ለድርጅቱ እና ለጎብኝዎች ጠቃሚ መሆኑን ገልጸዋል።
በአንድ ወቅት የፊፋ ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩት ብላተር ፊፋ ኳታር የ2022ን የአለም ዋንጫ እንድታስተናግድ መፈቅዱን ተችተው ነበር። ብላተር ኳታር ትንሽ ስለሆነች ማስተናገድ አትችልም በሚል ነበር የፊፋን ውሳኔ የነቀፉት።
ብላተር በ2030፣ 100አመት የሚሞላው የዓለም ዋንጫ የመጀመሪያውን ውድድር ባዘጋደችው እና ባነሳችው ኡራጓይ መካሄድ አለበት ብለዋል።
ብላተር እንደተናገሩት "ታሪካዊ በሆነ ምክንያት የ2030 የዓለም ዋንጫ በደቡብ አሜሪካ መካሄድ አለበት"።