ስፖርት
በፊፋ የደረጃ ስንጠረዥ ምርጥ 10 የአፍሪካ ብሄራዊ ቡድኖች የትኞቹ ናቸው?
በሰኔ ወር የደረጃ ሰንጠረዥ ሞሮኮ ከአፍሪካ 1ኛ ከዓለም 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች
ፊፋ የሰኔ ወር የሀገራት የደረጃ ሰንጠረዥን ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ አርጀንቲነ ከዓለም ቀዳሚ ናት
ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳደሪ አካል (ፊፋ) የሰኔ ወር የሀገራት የደረጃ ሰንጠረዥን ከሰሞኑ ይፋ አድርጓል።
በሰኔ ወር የደረጃ ሰንጠረዡ አርጀንቲና ከዓለም 1ኛ ስትሆን፤ ፈረንሳይ፣ ብራዚል፣ እንግሊዝና ቤልጂየም በቅደም ተከተላቸው ከ2ኛ እስከ 5ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።
ሞሮኮ ከአፍሪካ 1ኛ ከዓለም 13ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን፤ ከዓለም 18ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ሴኔጋል ከአፍሪካ 2ኛ፣ ከዓለም 31ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ቱኒዚያ ከአፍሪካ 3ኛ ደረጃን ይዛለች።
ኢትዮጵያ በፊፋ የሰኔ ወር የደረጃ ሰንጠረዥ ከዓለም 143ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን፤ ከአፍሪካ ደግሞ 42ኛ ደረጃን ይዛለች።