ማህበሩ 7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘት በሚያስችለው ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ዋና ጸሃፊው ተናግረዋል
ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማህበር (ፊፋ) 7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘት በሚያስችለው ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ዋና ጸሃፊው ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ተናገሩ፡፡
ፊፋ እስከተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት (2022) 6 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ ለማግኘት አቅዶ ነበር፡፡ ሆኖም ዋና ጸሃፊው ተጨማሪ 600 ሚሊዮን ዶላር በማግኘት 7 ቢሊዮን ዶላር ማትረፍ በምንችልበት የገቢ አቋም ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡
የማህበሩ የበጀት ዑደት በዓለም ዋንጫዎች መካከል በሚኖሩ አራት ዓመታት የሚታሰብ ነው፡፡ የሚጠበቀው 7 ቢሊዮን ዶላር ትርፍም ኳታር የምታዘጋጀውን የዘንድሮውን የዓለም ዋንጫ ያካትታል፡፡ ገቢው ከተለያዩ የስርጭት መብቶች እና ግብይቶች መገኘቱን ኢንፋንቲኖ ዛሬ ለተጠናቀቀው የማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ ተናግረዋል፡፡
ለዓለም ዋንጫ ማለፋቸውን ያረጋገጡ ሀገራት እነማን ናቸው?
ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት (2021) ከቀዳሚው ዓመት የ266 ሚሊዮን ዶላር ብልጫ ያለው 766 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አግኝቷል፡፡ ይህ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የዓለምን ምጣኔ ሃብት ባዳከመበት የተገኘ ነው፡፡ እስካሳለፍነው ታህሳስ ደረስም በጥቅሉ በአራቱ ዓመታት ውስጥ ለማግኘት ካቀደው ገቢው ውስጥ አብላጫውን (6 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር) ለማግኘት ችሏል፡፡
ማህበሩ አብዛኛውን ገቢ የሚያገኘው በየአራት ዓመቱ ከሚመጡት የዓለም ዋንጫዎች መሆኑን ተከትሎ የዘንድሮ ገቢው ከቀደሙት ዓመታት ከፍ ሊል እንደሚችል ተገምቷል፡፡
ገቢው በወረርሽኙ የተጎዳውን የእግር ኳስ ውድድሮች ለማነቃቃት እና የማህበሩን የፋይናንስ አቅም ለማሳደግ እንደሚውልም ተገልጿል፡፡
ጣሊያን ከ2022ቱ የዓለም ዋንጫ ውጭ መሆኗን ተከትሎ በአዙሪዎቹ ቤት ሃዘን ነግሷል
ሆኖም በተለይ የቴሌቪዥን የስርጭት መብቶች በከፍተኛ ዋጋ መሸጥ ከጀመረ በኋላ በገቢ እጦት የማይታማው ፊፋ በሙስና እና ተያያዝ ቅሌቶች ስሙ ተጠቃሽ ነው፡፡
የቀድሞው የማህበሩ ፕሬዝዳንት ሴፕ ብላተር ከእንዲሁ ዐይነት ድርጊቶች ጋር በተያያዘ በህግ መጠየቃቸው ይታወሳል፡፡