ፊፋ አርጀንቲና ያቀረበችውን ቅሬታ ወድቅ አደረገ
አርጀንቲና ባለፈው ረቡዕ እለት የተካሄደውን የወንጆች የኦሎምፒክ እግርኳስ ውድድር በሞሮኮ 2-1 ተሸንፋለች
" ኤኤፍኤ እንዲህ አይነት ውሳኔ በምን አግባብ እንደተወሰነ እንደጠይቃለን" ብለዋል ታፒያ።
ፊፋ አርጀንቲና ያቀረበችውን ቅሬታ ወድቅ አደረገ።
አለምአቀፉ የእግርኳስ ፌደሬሽን(ፊፋ) አርጀንቲና ከሞሮኮ ጋር ባደረገችው የኦሎምፒክ የመክፈቻ ጨዋታ ወቅት በመጨረሻ ደቂቃ ካስቆጠረቻት ጎል ጋር በተያያዘ ያቀረበችውን አቤቱታ ውድቅ ማድረጉን የአርጀንቲና እግርኳስ ፌደሬሽን(ኤኤፍኤ) አስታውቋል።
"የፊፋ የስነ ስርአት ኮሚቴ ከሞሮኮ ጋር በተደረገው ጨዋታ ወቀት የነበረውን ክስተት በተመለከት የቀረበውን ቅሬታ ውድቅ አድርጎታል" ሲሉ የኤኤፍኤ ፕሬዝደንት ክላውዶ ታፒያ በኤክስ ገጻቸው ጽፈዋል።
አርጀንቲና ባለፈው ረቡዕ እለት የተካሄደውን የወንጆች የኦሎምፒክ እግርኳስ ውድድር በሞሮኮ 2-1 ተሸንፋለች።
ደጋፊዎች ወደ ሜዳ በመግባታቸው ምክንያት ጨዋታው 2-2 ተቋርጦ የነበረ ቢሆንም ከሰአታት በኋላ ቪዲዮ አሲስታንስ ሪፈሪ(ቫር) የአርጀንቲናን ጎል ውድቅ አድርጓታል። የፓሪስ ኦሎምፒክ አዘጋጆች ደጋፊዎቹ ወደ ሜዳ ጥሰው እንዲገቡ ያደረጋቸው ምክንያት ምን እንደሆነ ለመወሰን እየሰራ እንደሆነ ባለፈው ሀሙስ ገልጾ ነበር።
" ኤኤፍኤ እንዲህ አይነት ውሳኔ በምን አግባብ እንደተወሰነ እንደጠይቃለን" ብለዋል ታፒያ።
ስኬታማው የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን በኳታር አስተናጋጅነት የተዘጋጀውን የ2022ቱን የአለም ዋንጫ እና ኮሎምቢያን በማሸነፍ አህጉራዊውን የኮፓ አሜሪካ ዋንጫ ለ16ኛ ጊዜ አንስቷል። የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድንም በዚሁ የአለም ዋንጫ 4ኛ ሆኖ ማጠናቀቅ የቻለ ጠንካራ ቡድን ነው።