ፊፋ እስራኤልን ከፍልስጤም ጋር በተያያዘ ከእግር ኳስ ውድድሮች ያግድ ይሆን?
ፍልስጤም እራኤል በጋዛ የጦር ወንጀል ፈጽማለች በሚል ከየትኛውም የእግር ኳስ ውድድሮች እንድትታገድ ጠይቃለች
ፊፋ በጉዳዩ ዙሪያ ውሳኔ ለማሳለፍ የፊታችን ሀምሌ አጋማሽ ይሰበሰባል
ፊፋ እስራኤልን ከፍልስጤም ጋር በተያያዘ ከእግር ኳስ ውድድሮች ያግድ ይሆን?
ሀማስ ከሳባት ወር በፊት በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት መክፈቱን ተከትሎ የተጀመረው ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል።
ይህን ተከትሎ እስራኤል በሀማስ ስም በንጹሀን ዜጎች ላይ ጥቃት በመክፈት ከ35 ሺህ በላይ ንጹሃንን በመግደል የጦር ወንጀል ፈጽማለች በሚል ፍልስጤምን ጨምሮ በርካታ ሀገራ እየተናገሩ ናቸው፡፡
ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ወይም ፊፋ እስራኤል ከየትኛውም እግር ኳስ ውድድሮች እንድትታገድ በይፋ ከፍልስጤም ጥያቄ ቀርቦለታል፡፡
የፍልስጤም እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለፊፋ ባቀረበው አቤቱታ እስራኤል በጋዛ የሚገኙ የእግር ኳስ መሰረተ ልማቶችን ሆን ብላ አውድማለች ሲል ከሷል፡፡
ፊፋም ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት የፊታችን ሀምሌ 18 ቀን 2016 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤውን ለማካሄድ ቀነ ቀጠሮ መያዙን አስታውቋል፡፡
ፊፋ 'ሰማያዊ ካርድ'ን እንደሚቃወም ኢንፋንቲኖ ተናገሩ
ይሁንና ፊፋ የ211 አባል ሀገራት ተወካዮቹ ይህን ውሳኔ ከማስተላለፋቸው በፊት የህግ ባለሙያዎችን አስተያየት እፈልጋለሁ ብሏል፡፡
የፊፋ ዋና ጸሀፊ ጂያን ኢንፋንቲኖ እንዳሉት በፍልስጤም ለቀረበልን ጥያቄ ምላሽ እንድንሰጥ ገለልተኛ የህግ ኩባንያዎች አስተያየት መስማት ይኖርብናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የፍልስጤም ጥያቄ የፊፋ መወያያ አጀንዳ እንዲሆን አልጀሪያ፣ ኢራቅ፣ ጆርዳን ሶሪያ እና የመን እንደደገፉት ተገልጿል፡፡
እስራኤል እስካሁን የፍልስጤም የስፖርት መሰረተ ልማቶችን አውድማለች በሚል ለፊፋ በቀረበባት ክስ ዙሪያ ከመናገር ተቆጥባለች፡፡