ፊሊፒንስ የወባ ትንኝ ለሚይዙ ዜጎቿ ሽልማት አዘጋጀች
የወባ ትንኞቹ ከነ ህይወታቸው ሆነ ሞተው ቢያዙ ችግር የለም ብላለች

ሀገሪቱ አምስት የወባ ትንኝ መያዝ ለቻለ ሰው አንድ የፊሊፒንስ ፔሶ እንደምትሸልም አስታውቃለች
ፊሊፒንስ የወባ ትንኝ ለሚይዙ ዜጎቿ ሽልማት አዘጋጀች
በወባ በሽታ በርካታ ዜጓን የምታጣው እስያዊቷ ፊሊፒንስ የወባ ትንኝ አድነው ለሚይዙ ዜጎች ሽልማት አዘጋጅታለች፡፡
ዴንጊ በተሰኘው የወባ ወረርሽኝ የተጠቃችው ፊሊፒንስ ለበሽታው መነሻ የሖነችው የወባ ትንኝ ላይ ዘመቻ ጀምራለች፡፡
በዚህም መሰረት አምስት የወባ ትንኝ ለያዘ ሰው አንድ ፔሶ ወይም 0 ነጥብ 2 ዶላር እንደምትሸልም አስታውቃለች፡፡
ይሁንና የሀገሪቱ አዲስ የወባ ትንኝ አደን ዘመቻ በመላው ሀገሪቱ ወደ ቀልድነት ተቀይሯል የተባለ ሲሆን በርካቶች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተሳለቁ እንደሆነ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የሀገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ግን የወባ ትንኝ አደን ዘመቻው ከኬሚካል ርጭት እና ህክምና በተጨማሪነት የተያዘ እቅድ እንጂ ቀልድ አይደለም ብሏል፡፡
በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ከተሰራጩ ቀልዶች መካከልም የወባ ትንኞቹን ለመያዝ ስንሞክር የአካል መጉደል ቢያጋጥም ክፍያው ይቀንስብን ይሆን፣ ፊሊፒንስ የወባ ትንኝ ኢንቨስትመንት ጀመረች እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡
በትናንትናው ዕለት ሁለት የዩንቨርሲቲ ተማሪዎች በዚሁ ወባ መሳይ ደንጊ ወረርሽኝ ምክንት ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
የካቲት ወር ከገባ ጊዜ ጀምሮ ከ28 ሺህ በላይ ሰዎች በደንጊ ወረርሽኝ ሲጠቁ ስርጭቱ ከአምናው ጋር ሲነጻጸር የ40 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡