አዲስና ውጤታማ የሆነ የወባ መከላከያ ክትበት መገኘቱ ተገለጸ
የመጨረሻ የሙከራ ሂደት የሚቀረው ክትባቱ አሁን ባለው ደረጀ 80 በመቶ ውጤታማ ነው
የወባ ክትባቱ በቡርኪናፋሶ በሚገኙ ከ400 በላይ ህጻናት ላይ ተሞክሯል
ውጤታማ የሆነ አዲስ የወባ መከላከያ ክትባት ማግኘታቸውን ተመራማሪዎች ከሰሚኑ አስታውቀዋል።
ክትባቱን የህንዱ ሲረም ኢኒስቲትዩት ከእንግሊዙ ኦክፎርድ ዩኒሸርሲቲ ጋር በጋራ በመሆን መስራታቸው ተነግሯል።
አዲሱ የወባ ክትባት በአፍሪካ ሀገራት በሚገኙ ህጻናት ላይ ሙከራ ሲደረግ የነበረ ሲሆን በዚህም 80 በመቶ ውጤታማ መሆን መቻሉ ነው የተገለጸው።
በክትባቱ ሙከራ ላይ 450 የበከርኪና ፋሶ ህጻናት የተሳተፉ ሲሆን፣ ለህጻናቱም በየአራት ሳምታት ልዩነት ሶስት ክትባቶች እንዲሁም ከ12 ወራት ቖይታ በሁዋላ ቡስተር እንዲከተቡ ተደርጓል።
በዚህም አዲሱ የክትባት እስካሁን ባለው ሂደት 80 በመቶ ውጤታማ ነው የተባለ ሲሆን፣ ከአንድ የመጨረሻ ሙከራ በሁዋላ ጥቅም ላይ መዋል እንደሚጀምር ይጠብቃል።
አዲሱ የወባ መከላከያ ክትባት በቀጣዩ የፈረንጆቹ 2023 ለተጠቃሚዎች መድረስ ሊጀምር እንደሚችልም በክትባቱ ላይ እየሰሩ ያሉ ተቁዋማት አስታውቀዋል።
ክትባቱ ረረጥቅም ላይ መዋል ሲጀምርም የህንዱ ሲረም ኢኒስቲትዩት ከእንግሊዙ ኦክፎርድ ዩኒሸርሲቲ በጋራ በመሆን በየዓመቱ 200 ሚሊየን ክትባቶችን ያመርታሉ ተብሏል።