ለአለም ስጋት ለሆነው ወባ ተጠያቂው ማን ነው?
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በወባ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል
የአየር ንብረት ለውጥ ነው ለወባ በሽታ መስፋፋት ዋኛው ተጠያቂ ነው ተብሏል
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በወባ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል።
በብዙ ምክንያቶች የአየር ንብረት ለውጥ በወባ ስርጭት ውስጥ ትልቅ ሚና ይጫወታል።
እንደ አለም ጤና ድርጅት ዘገባ ከሆነ በጎርጎሮሳዊያኑ 2021 ከዓለም ህዝብ ግማሽ ያህሉ ለወባ የተጋለጠ ሲሆን፤ በዚሁ ዓመት የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር 247 ሚሊዮን ደርሷል።
ከነዚህም ውስጥ 619 ሽህ ያህሉ ህይወታቸው አልፏል። ድርጅቱ አፍሪካ በዓለም ትልቁን ድርሻ እንደምትይዝ ያምናል። በ2021 95 በመቶ ያህሉ በበሽታው የተያዙ እና 96 በመቶው ሞት ሰዎች በአህጉሪቱ ነው።
የአየር ንብረት ለውጥ እና የዝናብ ሁኔታ ለውጥ ወባ ተሸካሚ ትንኞች መራባት እና መስፋፋት እንዲጨምር ከማድረግ በተጨማሪም አዳዲስ አካባቢዎች መታየት፣ ረዘም ላለ ጊዜ መቆየት መቻላቸው ስፋቱን ይጨምራል።
የዓለም የጤና ድርጅት አስቀድሞ ምርመራ ማድረግን ይመክራል።
ምክንያቱም ህክምናው ከባድ ህመም እና ሞትን በመከላከሉ እንዲሁም የወባ ስርጭትን ስለሚገድብ ነው።
አብዛኛው የወባ ተጠቂነት እና ሞት እንደ አፍሪካ ባሉ ታዳጊ ሀገራት የሚከሰተው በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ነው።
የወባ ትንኞች በአፍሪካ አየር ንብረት ውስጥ በህይወት ሊቆዩ እና ሊራቡ ስለሚችሉ፣ በተጨማሪም የጤና በጀት አነስተኛ መሆን እና ቀጣይነት ያለው የሀብት ብዝበዛ በምክንያትነት ይጠቀሳሉ።
ሞቃታማ አየር ንብረት ምግብ፣ ውሃ እና ተላላፊ በሽታዎች እንዲሰራጩ ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል። ይህም ቀደም ሲል ያልተጋለጡ ሰዎች ላይ በሽታዎችን በማምጣት እንዲሁም በዓለም አቀፍ የህብረተሰብ ጤና ላይ ለአስርተ ዓመታት የተመዘገበውን እድገት ያወርዳል።