አሜሪካ የሰሜን ኮሪያን የኒውክር ሙከራ የማስቆም አቅም ያላቸው ሩሲያ እና ቻይና ናቸው አለች
አሜሪካ፣ሰሜን ኮሪያ ከ2017 ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የኒውክሌር ሙከራ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኗን ገልጻለች
ሰሜን ኮሪያ ሚሳይል መተኮሷን ተከትሎ አሜሪካና እና ደቡብ ኮሪያ ሲያካሂዱት የነበረውን ወታደራዊ ልምምድ አራዝመዋል
አሜሪካ፣ ቻይና እና ሩሲያ የሰሜን ኮሪያን የኒውክሌር ሙከራን ለማስቆም የሚያስችል አቅም እንዳላቸው ገለጸች፡፡
አንድ የአሜሪካ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን እንደተናገሩት ቻይና እና ሩሲያ ሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር ሙከራዎችን እንዳትቀጥል ለማሳመን ሊጠቀሙበት የሚችሉበት አቅም አላቸው ብላ አሜሪካ እንደምታን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉት ሮይተርስ ያነጋገራቸው ባለስልጣኑ ሰሜን ኮሪያ ከ2017 ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የኒውክሌር ሙከራ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኗን ገልጸዋል፡፡
ደቡብ ኮሪያም ሰባተኛውን የኒውክሌር ሙከራ ለማድረግ ለወራት ስታስጠነቅቅ የቆየች ሲሆን የተባበሩት መንግስታት የኒውክሌር ተቆጣጣሪ ባለፈው ሳምንት ሰሜን ኮሪያ ለሙከራ እየተዘጋጀች ነው ብሏል።
የአሜሪካው ባለስልጣን “ዝግጅት ማድረጋቸውን በጣም እርግጠኞች ነን። ይህን ሊያደርጉ እንደሚችሉ እናምናለን… ሲሉ ተናግረዋል፡፡
"እነሱ (ሰሜን ኮሪያ) በክልሉ ውስጥ ለሌሎች የተጋላጭነት ደረጃ ስሌት እየሰሩ ነው ብለን እናስባለን፡፡ እንደማስበው በተለይም ሩሲያ እና ቻይና በእነሱ አመለካከት ላይ ተጽእኖ አለው" ብለዋል፡፡
ሰሜን ኮሪያ በኒውክሌር ሙከራዎችን እና የባለስቲክ ሚሳኤልን ማስወንጨፍ በተመድ የጸጥታው ም/ቤት መከልከሏ ይታወሳል፡፡ ነገርግን 15 አባላት ባሉት የጸጥታው ም/ቤት ያለው አለመግባባት በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ስለተባባሰ በሰሜን ኮሪያ ላይ በያዘው ጉዳይ ላይ ከስምምነት አልደሰም፡፡
በግንቦት ወር ሩሲያ እና ቻይና በ 2017 ጠንካራ ማዕቀቦችን ከደገፉ በኋላ ፒዮንግያንግ ባደረገችው የባሊስቲክ ሚሳኤል ሙከራ ምክንያት በአሜሪካ የሚመራው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተጨማሪ ማዕቀቦችን ለመጣል የተደረገውን ሙከራ በቬቶ ውድቅ አድርገዋል።
ሰሜን ኮሪያ ሚሳይል መተኮሷን ተከትሎ አሜሪካና እና ደቡብ ኮሪያ ሲያካሂዱት የነበረውን ወታደራዊ ልምምድ ማራዘማቸውን ገልጸዋል፡፡