የአውሮፓ ግማሹ ህዝብ የጤና ማገገሚያ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ
በአውሮፓ እና እስያ ያሉ 394 ሚሊዮን ዜጎች የማገገሚያ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ተገለጸ
በሁለቱ አህጉራት በእድሜ የገፉ ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት ገልጿል
በአውሮፓ እና እስያ ያሉ 394 ሚሊዮን ዜጎች የጤና ማገገሚያ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው የዓለም ጤና ድርጅት ገለጸ፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት እንደገለጸው በአውሮፓ እና እስያ በእድሜ የገፉ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ተከትሎ የማገገሚያ ድጋፍ የሚፈልጉ ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን አስታውቋል፡፡
በተለይም በአውሮፓ ግማሽ ያህሉ የሕዝብ በዛት በእድሜ የገፋ ማህበረሰብ መሆኑን ተከትሎ በጽኑ ህመም የተያዙ እና የጤና ማገገሚያ ድጋፎችን እንደሚፈልጉ ድርጅቱ አስታውቋል፡፡
በዓለም ጤና ድርጅት የአውሮፓ እና ማዕከላዊ እስያ ቢሮ ባወጣው ሪፖርት 394 ሚሊዮን ዜጎች የጤና ማገገሚያ ድጋፎች ያስፈልጋቸዋል ብሏል፡፡
እንደ ቢሮው ሪፖርት በሁለቱ አካባቢዎች የጤና ማገገሚያ ድጋፎችን የሚፈልጉ ዜጎች የጨመረው እድሜያቸው የገፉ ዜጎች ቁጥር መጨመር፣ በጽኑ ህመም የሚጠቁ ዜጎች ቁጥር መጨመር፣ የአመለካከት ችግሮች ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል፡፡
በዓለም ጤና ድርጅት የአውሮፓ ቢሮ ዳይሬክተር ሀንስ ክሉግ እንዳሉት ግማሹ የአውሮፓ ዜጋ የጤና ማገገሚያ ድጋፍ ይፈልጋል ያሉ ሲሆን ይህ በዚሁ ከቀጠለ ሀገራት ለማህበረሰቡ ጥቅም የማያበረክቱ ዜጎችን ከተለያዩ እድሎች እና አገልግሎቶች መገደብ ሊሞክሩ እንደሚችሉም አሳስበዋል፡፡
በመሆኑም የጤና መገገሚያ ማዕከላት ለሁሉም ዜጎች ክፍት ሊደረጉ ይገባል የሚሉት ዳይሬክተሩ አገልግሎቱ ለሁሉም ዜጎች ክፍት የማይደረግ ከሆነ በየዓመቱ 49 ሚሊዮን ዜጎች ህይወታቸው ሊያልፍ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል፡፡
በአውሮፓ የጀር ህመም፣ የመስማት እና የማየት ችግር፣ የደም መርጋት፣ የደም ግፊት፣ የመርሳት በሽታ እና ሌሎችም እየጨመሩ ያሉ በሽታዎች ናቸው ተብሏል፡፡