የሎስ አንጀለሱ ሰደድ እሳት አደጋ ወቅታዊ ሁኔታ ምን ይመስላል?
የእሳት አደጋ ሰራተኞች ከበረሃ የተነሳ ንፋስ ቢኖርም የሎስ አንጀለስ ከተማ ክፍሎችን ለሳምንታት ያወደሙትን ሁለት ግዙፍ ሰድድ እሳቶች በዛሬው እለት ባሉባት ማስቆም ችለዋል
በአደጋው የሞቱ ሰዎች ቁጥር በዛሬው እለት በአንድ ጨምሮ 25 መድረሱን ሮይተርስ የሎስ አንጀለስ ሜዲካል መርማሪ ቢሮን ጠቅሶ ዘግቧል
የእሳት አደጋ ሰራተኞች ከበረሃ የተነሳ ንፋስ ቢኖርም የሎስ አንጀለስ ከተማ ክፍሎችን ለሳምንታት ያወደሙትን ሁለት ግዙፍ ሰድድ እሳቶች በዛሬው እለት ባሉባት ማስቆም ችለዋል።
ቢያንስ ከሰባት የአሜሪካ ግዛቶች እና ከሁለት የውጭ ሀገራት የተውጣጡ 8500 የእሳት አደጋ ሰራተኞች እሳቱን እንዳይስፋፋ ለሁለተኛ ቀን እየተከላከሉ ነው።
በርካታ ጄቶች እሳቱ እንዳይስፋፋ የሚያደርገውን ሪተርዳንት ወይም እሳት ማዘግያ ኬሚካል እና ውሃ በኮረብታዎቹ ላይ እየረጩ ሲሆን በመሬት ላይ የተሰማሩት ቡድኖች ደግሞ እሳቱ ከተነሳበት ከባለፈው ጥቅምት 7፣2025 ጀምሮ ሌት ከቀን እነሰሩ ናቸው። ጄቶቹ አልፎ አልፎ በከባድ ንፉስ ምክንያት ለማረፍ ይገደዳሉ።
በከተማዋ ምዕራብ በኩል የተነሳው የፓሊሳደስ እሳት 96 ስኩየር ኪሎሜትር ስፋት ያለው ቦታ ያወደመ ሲሆን 18 ተገትቷል። ከምስራቅ የነተሳው የኢቶን እሳት ደግሞ 57 ስኩየር ኪሎሜትር ስፋት ያለው ቦታ ያቃጠለ ሲሆን የእሳት አደጋ ሰራተኞች እሳቱን እንዳይስፋፋ የማድረግ አቅማቸው 35 በመቶ አድጓል።
ከባለፈው ሚያዝያ ጀምሮ በቂ ዝናዝ ባለገኘችው ደቡባዊ ካሊፎርንያ ከበረሃ የተነሳው የሳንታ አና ንፋስ ወደ ተራራዎች እና ሸለቆዎች የእሳት ፍም እስከ 3 ኪሎሜትር ድረስ ይዞ ይጓዛል። በዛሬው እለት የንፋሱ ጥንካሬ የደከመ ቢሆንም ሊጨምር እንደሚችል ትንበያዎች ያመለክታሉ።
በአደጋው የሞቱ ሰዎች ቁጥር በዛሬው እለት በአንድ ጨምሮ 25 መድረሱን ሮይተርስ የሎስ አንጀለስ ሜዲካል መርማሪ ቢሮን ጠቅሶ ዘግቧል። በአደጋው 12ሺ ገደማ ህንጻዎች ወይም ቤቶች በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ እንደወደሙ ይገመታል። ሙሉ መንደር ወድሞ በአመድ እና በፍርስራሽ ተሞልቷል።
በአደጋው ምክንያት ተፈናቅለው ከነበሩት ውስጥ ጥቂት ሺዎች እንዲመለሱ ቢፈቀድም 88 ሺ የሚሆኑት አሁንም የተለየ ትዕዛዝ አልተሰጣቸውም።
በአደጋው የደረሰው ጠቅላላ ውድመት እና የኢኮኖሚ ኪሳራ 250 ቢሊዮን እና 275 ቢሊዮን ዶላር መሆኑን አኩ ዌዘር የገመተ ሲሆን በ2025 ሁሪካን ካትሪና ካደረሰው አደጋ በመብለጥ በአሜሪካ ታሪክ እጅግ ከባድ የተፈጥሮ አደጋ ሆኖ ተመዝግቧል።