በሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ መኖሪያ ቤቶችና ሌሎች ሕንፃዎች ተቃጥለዋል ተባለ
በግዙፉ የሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 10 ከፍ ብሏል
በእሳት አደጋው የደረሰው የኢኮኖሚ ጉዳት ወደ 150 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ማለቱ ተነግሯል
በአሜሪካ ሎሳንጀለስ ዙሪያ የተቀሰቀሰው ከባድ የሰደድ እሳት አደጋ አሁንም ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን እንደቀጠለ ነው።
ሎስ አንጀለስን ከምስራቅ እና ከምዕራብ እያነደደ ያለው ሁለት ግዙፍ ሰደድ እሳት ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ መኖሪያ ቤቶችን እና ሌሎች ግንባታዎችን በልቷል ነው የተባለው።
በዚህም በምስራቅ ፓሳዴና አቅራቢያ የሚገኘው ኢቶን እሳት ከ4 ሺህ እስከ 5 ሺህ የሚሆኑ መኖሪያ ቤቶችና ህጻዎችን ማውደሙ ተነግሯል።
በሳንታ ሞኒካ እና በማሊቡ መካከል ያለው የፓሊሳዴስ እሳት ድገሞ 5 ሺህ 300 ገደማ መኖሪያ ቤቶች እ ህንጻዎችን ማውደሙ ነው የተገለጸው።
በሳንታ ሞኒካ እና በማሊቡ መካከል ያለው የፓሊሳዴስ እሳት እንዲሁም በከተማው ምዕራባዊ ዳርቻ እና በምስራቅ ፓሳዴና አቅራቢያ የሚገኘው ኢቶን እሳት በሎስ አንጀለስ ታሪክ ውስጥ እጅግ አጥፊ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፤ 13 ሺህ 750 ሄክታር ማቃጠሉን እና የመኖሪያ ሰፈሮችን በሙሉ ወደ አመድነት መቀየሩ ተነግሯል።
በእሳት አደጋው ህይወታቸው ያለፈ ቁጥር ወደ 10 ከፍ ማቱም የተነገረ ሲሆን፤ የሰደድ እሳቲ ካስከተለው ውድት አንጻር የሟቾች ቁጥር ሊያሻብ እንደሚችል ተገምቷል።
አኩ ዌዘር የተባለው የግል የትንበያ ተቋም በእሳት አደጋው የደረሰው የኢኮኖሚ ጉዳት ከ137 እስከ 150 ቢሊየን ዶላር በላይ እንደሚገመት ገልጿል።