በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው ተገኘ
በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው ተገኘ
ግብፅ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው በሀገሪቱ መኖሩን ያረጋገጠች ሲሆን፣ ቫይረሱ የተገኘበት ሰው በሆስፒታል ውስጥ ተለይቶ እየታከመ እንደሚገኝ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ወዲያውኑ ለአለም ጤና ድርጅት ማሳወቁንና አስፈላጊ የመከላከል እርምጃ እንደወሰደም ገልጿል፡፡
በቫይረሱ ተያዘ የተባለው ግለሰብ የውጭ ሀገር ዜጋ ነው ያለው ሚኒስቴሩ የየት ሀገር ዜጋ እንደሆነ ግን አላስታወቀም፡፡ በግብፅ ቫይረሱ መኖሩ ሲረጋገጥ በአፍሪካም የመጀመሪያ ሆኗል፡፡