አንዳንድ የልማት ባንኮች የድሀ ሀገራትን የብድር ጫና እያባባሱ ነው - የአለም ባንክ ኃላፊ
አንዳንድ የልማት ባንኮች የድሀ ሀገራትን የብድር ጫና እያባባሱ ነው - የአለም ባንክ ኃላፊ
የአለም ባንክ ፕሬዘዳንት ዴቪድ ማልፓስ ሌሎች ልማት ባንኮች ከፍተኛ የብድር ጫና ላለባቸው ሀገራት በፍጥነት በማበደራቸው ምክንያት፣ ሀገራቱ ቀድሞ ያለባቸውን የብድር ጫና እያባባሱባቸው ይገኛሉ ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ማልፓስ የአለም ባንክና ኢንተርናሽናል ሞናተሪ ፈንድ ባዘጋጁት የብድር ፎረም ላይ የኤሲያ፣ የአውሮፓና የአፍሪካ የልማት ባንኮች ለብድር ጫና ችግር አስተዋጽኦ እያደረጉ ነው በማለት ተችተዋል፡፡
“አሁን ያለንበት ሁኔታ ሌሎች የአለም አቀፍ የብድር ተቋማትና በተወሰነ ደረጃም ቢሆን የልማት ፋይናንስ ተቋማት ቶሎ የማበደር ዝንባሌ ያላቸው መሆኑ በሀገራት የብድር ጫና ችግር ይጨምራል” ብለዋል ማልፓስ፡፡
የኤሲያ ልማት ባንክ ቢሊዮን ዶላሮችን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ላላችው ፓኪስታን ያበድራል፤ የአፍሪካ ልማት ባንክ ደግሞ በደቡብ አፍሪካና በናይጀሪያ ተመሳሳይ ነገር እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ስለትችቱ የኤሲያ ልማት ባንክ ቃል አቀባይ ለማግኘት አልተቻለም ሮይተስ አስነብቧል፡፡