አሜሪካን ጨምሮ አምስት ሀገራት የባህር ላይ ጦርነት ልምምድ ጀመሩ
በጦር ልምምድ ፕሮግራሙ ላይ አሜሪካ፣ ሲንጋፖር፣ አውስትራሊያ ፣ ኢንዶኔዥያ እና ጃፓን በመሳተፍ ላይ ናቸው
በሱማትራ ባህር ላይ በተጀመረው በዚህ የጦር ልምምድ ከአራት ሺህ በላይ ወታደሮች በመሳተፍ ላይ ናቸው
አሜሪካን ጨምሮ አምስት ሀገራት የባህር ላይ ጦርነት ልምምድ ጀመሩ።
በአሜሪካ ባህር ኃይል አስተባባሪነት አምስት ሀገራት በኢንዶኔዥያዋ ሱማትራ ባህር ላይ የጦርነት ልምምድ እየተካሄደ እንደሆነ ሮይተርስ ዘግቧል።
በዚህ የባህር ላይ ጦርነት ልምምድ አሜሪካን፣ አውስትራሊያ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ሲንጋፖር እና የጃፓን ወታደሮች በድምሩ ከአራት ሺህ በላይ የባህር ላይ ወታደሮች በመሳተፍ ላይ ናቸውም ተብሏል።
ከባህር ላይ ጦርነት ልምምዱ እስያን እየጎበኘች ያለችው የአሜሪካ አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ወደ ታይዋን ምድር እንዳይመጡ ማስጠንቀቂያ ከተሰጠ በኋላ እየተካሄደ ይገኛል።
አሜሪካ በዚህ የባህር ላይ ጦርነት ልምምድን አስመልክቶ እንዳለችው ልምምዱ ማንንም ለማስፈራራት ታስቦ የተዘጋጀ አይደለም፣ አላማው የአካባቢውን ሀገራት ትብብር ለማጠናከር ያለም መሆኑን አስታውቃለች።
ይህ የጦርነት ልምምድ ለቀጣዮቹ 14 ቀናት እንደሚቀጥል የተገለጸ ሲሆን ጃፓን በዚህ ልምምድ ላይ ስትካፈል ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሆነም ተገልጿል።
በዚህ ልምምድ ላይም ፈረንሳይ፣ ካናዳ፣ ህንድ፣ ማሌዥያ እና ደቡብ ኮሪያ፣ ብሪታንያ፣ ፓፓ ኒውጊኒ እና ኢስት ቱመር በድምሩ አምስት ሀገራት ደግሞ በታዛቢነት በመሳተፍ ላይ ናቸው ተብሏል።