በቻይና የማዕድን ማውጫ አደጋ አምስት ሰዎች ሲሞቱ 48 ሰዎች ደግሞ ያሉበት አልታወቀም
300 የነፍስ አድን ሰራተኞች ማዕድን ቆፋሪዎችን ለማትረፍ እየሰሩ ነው ተብሏል
ማዕድን ቆፋሪዎች በግማሽ ኪሎ ሜትር ስፋት እና 80 ሜትር ከፍታ ባለው ግዙፍ የቆሻሻ ክምር ስር መቀበራቸው ተነግሯል
በቻይና የማዕድን ማውጫ አደጋ አምስት ሰዎች ሲሞቱ 48 ሰዎች ደግሞ ያሉበት አልታወቀም።
በቻይና ሰሜን ሞንጎሊያ ክልል የከሰል ማዕድን ማውጫ ተደርምሶ ቢያንስ አምስት ሰዎች ሲሞቱ 48 ሰዎች ደግሞ እስካሁን መጥፋታቸው ተግሯል።
ዢንጂንግ ከሰል አውጪ የተባለ ኩባንያ በቆሻሻ መደርመስ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰራተኞች በግማሽ ኪሎ ሜትር ስፋት እና 80 ሜትር ከፍታ ባለው ግዙፍ የቆሻሻ ክምር ስር እንዲቀበሩ ሆኗል ነው የተባለው።
ከማዕድን ማውጫው የተገኘ የደህንነት ምስል ተራራው ጥግ ላይ የነበረ የድንጋይ እና የአፈር ናዳ በርካታ ቁፋሮዎችን እና ገልባጭ መኪናዎችን ሲቀብር ያሳያል።
300 የነፍስ አድን ሰራተኞች ማዕድን ቆፋሪዎችን ለማትረፍ ከባድ ማሽነሪዎችን እና አዳኝ ውሾችን እየተጠቀሙ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
በቻይና የድንጋይ ከሰል ዋነኛ የኃይል ምንጭ ሲሆን፤ ማዕድን ማውጫዎቹ ደግሞ በዓለም ላይ እጅግ አደገኛ ከሆኑት መካከል ናቸው ተብሏል።
ማውጫዎቹ በዋነኛነት በዝቅተኛ የደህንነት መመሪያዎችን የሚከተሉ መሆን፤ የሀገሪቱ መንግስት ለዓመታት የደህንነት መሻሻል እንዲደረግ ትእዛዝ መስጠቱ ተገልጿል።