የደቡብ አፍሪካ የራግቢ ተጫዋቾች በኮቪድ ምክንያት ከቶኪዮ ኦሎምፒክ መንደር ውጭ ሆኑ
አምስቱ የራግቢ ተጨዋችዎቹ እስከ መጪው አርብ በቶክዮ አንድ ሆቴል ይቆያሉም ተብሏል
የደቡብ አፍሪካው የራግቢ ቡዱን በቶክዮ ኦሎምፒክ ወርቅ ያመጣል ተብለው ከሚጠበቁ ቡዱኖች አንዱ ነው
አምስት የደቡብ አፍሪካ የራግቢ ሰባት ቡዱን ተጫዋቾች በቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ መንደር ውስጥ እንደማይቆዩ ተገለጸ፡፡
አሰልጣኝ ኒል ፓውል ባለፈው ሳምንት ጃፓን ሲደርሱ በተደረገላቸው ምርምራ በኮቪድ መያዛቸውንና ራሳቸው አግለው እንደሚገኙና ከሸኞ እስከ እሮብ የሚደረጉ ውድድሮች በቪድዮ እንደሚመለከቱ መገለጹ የሚታወቅ ነው፡፡
እናም አሁን ላይ ከኦሎምፒክ መንደር ውጭ የሆኑት ተጫዋቾች ከአሠልጣኙ ኒል ፓውል ጋር ቅርብ ግንኙነት አለቸው የተባሉት መሆናቸውን ነው ባለስልጣናት ገለጹት፡፡
የተጨዋቾቹ ከኦሎምፒክ መንደር ውጭ መሆን ለወርቅ ይፎካከራል በተባለው ቡዱን እያደረገ ባለው ቅድመ ዝግጅት ከፍተኛ ተጽእኖ ይፈጥራል ተብሏል፡፡
እንደ ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘገባ ከሆነ ስማቸው ያልተገለጸው አምስቱ የራግቢ ተጨዋችዎቹ እስከ መጪው አርብ በቶክዮ አንድ ሆቴል የሚቆዩ ይሆናል፡፡
ረዳት አሰልጣኙ ሬንፍሬድ ዳዜል ሁኔታውን በማስመልከት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “ምንም የምናደረገው ነገር የለም፤ የግድ ማድረግ ስላለብን ነው,” ብሏል፡፡
ነገሮች ቢከብዱም ከመፃንበጽ ጊዜ አንስቶ ነገሮች ተቋቁመን ለመስራት ሞክረናል፤ በዚህም መላው የቡዱኑ አባላት ምስጋና ይገናቸዋል ሲሉም አክሏል ረዳት አሰልጣኙ ሬንፍሬድ ዳዜል፡፡
የደቡብ አፍሪካ ቡዱን በራግቢ ጨዋታ ወርቅ ያመጣል ተብለው ከሚጠበቁ ቡዱኖች አንዱ ሲሆን ከአምስት አመታት በፊት በሪዮ ዴ ጃኔሪ ኦሎምፒክ ነሃስ ሜዳያ ማምጣቱ ይተወሳል፡፡