የሊቢያ ፍርድ ቤት የጋዳፊ ልጅ ወደ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውድድር እንዲመለሱ ወሰነ
የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን ሳኢፍ አል ኢስላም ጋዳፊ ከሊቢያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዕጩነት ሰርዞ ነበር
የሊቢያ ምርጫ በፈረንጆቹ ታህሳስ 24 ቀን 2021 ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል
የቀድሞ የሊቢያ መሪ መአማር ጋዳፊ ልጅ ሳኢፍ አል ኢስላም ጋዳፊ በሊቢያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዕጩነታቸው እንደመለሱ የሊቢያ ፍርድ ቤት ወሰነ።
የሊቢያ ምርጫ ኮሚሽን ሳኢፍ አል ኢስላም ጋዳፊን ጨምሮ ለምርጫው ሊወዳደሩ የነበሩ 25 ሰዎች ከምርጫው ውጭ እንዲሆኑ ወስኖ እንደነበረ ይታወሳል። ይህንን ተከትሎም ሳኢፍ አል ኢስላም ጋዳፊ የምርጫ ኮሚሽኑን ውሳኔ በመቃወም በደቡባዊ ሊቢያዋ ሴባህ በሚገኝ ፍርድ ቤት ይግባኝ ጠይቆ ነበር።
ፍርድ ቤቱም የቀድሞ የሊቢያ መሪ መአማር ጋዳፊ ልጅ ሳኢፍ አል ኢስላም ጋዳፊ በቀጣይ ወር በሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይ እንዲሳተፍ ውሳኔ አሳልፏል።
የሳኢፍ አል ኢስላምን ጉዳይ በተመለከተ ኮሚሽኑ የምርጫ ህጉ አንቀጾችን ጠቁሞ እጩ ተወዳዳሪ “በወረደ ወንጀል የተፈረደበት መሆን የለበትም” እና ንጹህ የወንጀል ሪከርድ ማቅረብ በሚለው ነበር ከምርጫው እጩነት ሰርዞ የነበረው።
የቀድሞ የሊቢያ መሪ የሙአማር ጋዳፊ ልጅ ሳኢፍ አል ኢስላም ጋዳፊ በሊቢያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ ከፍተኛ ተፎካካሪ እንደሚሆኑ ግምት ተስጥቷቸዋል።
ከወደ ምስራቅ ሊብያ የተገኙት ጠንካራው ካሊፋ ሃፍታር፣ ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልሀሚድ ዲቤባህ እና የቀድሞ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ፋቲ ባሻጋ በሊብያ ምርጫ የሚጠበቁ እጩዎች ናቸው።
ሁለቱም ፕሬዚዳንታዊ እና የህግ አውጭ ምርጫዎች ለታህሳስ 24 ተይዘው የነበረ ቢሆንም፤ በጥቅምት ወር መጀመሪያ ላይ ፓርላማው የድምጾቹን ቀናት በመከፋፈል የህግ አውጪ ምርጫዎችን እስከ ወርሃ ጥር ድረስ እንዲራዘም ማድረጉ አይዘነጋም።
በፈረንጆቹ ታህሳስ 24 ቀን 2021 ይካሄዳል ተብሎ ከሚጠበቀው ምርጫ በርካታ ዕጩዎች መሰረዛቸው ወደ ዴሞክራሲ ትጓዛለች ተብላ የምትጠበቀው ሊቢያን ወደሌላ ቀውስ እንዳይወስዳት ያሰጋል ተብሏል።
የሊቢያ ምርጫ ኮሚሽን 98 በመቶ የሚሆኑ እጩዎችን እንደመዘገበ መግለጹ ይታወሳል።