ባለሞያዎችና የረድኤት ድርጅቶች የጎርፍ አደጋውን መቀልበስ ይቻል ነበር ብለዋል
በጎርፍ በተመታው ምስራቅ ሊቢያ ደርና ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መንግስትን ተቃውመው አደባባይ ወጥተዋል።
የአካባቢውን አስተዳደር የተቹት ተቃዋሚዎች፤ ከ1 ሺህ በላይ ሰዎችን ለቀጠፈው የጎርፍ አደጋ መንግስትን ተጠያቂ አድርገዋል።
በደርና መሀል ከተማ በሚገኝ መስጊድ ላይ የተሰባሰቡት ተቃዋሚዎች፤ አደጋው በአፋጣኝ እንዲመረመር ጠይቀዋል።
ኃላፊነታቸውን ያልተወጡ የመንግስት ሹማምንትም በህግ ይጠየቁ ብለዋል።
ተቃዋሚዎች ለተጎጂዎች ካሳን ጨምሮ፤ የከተማዋ የፋይናንስ መዝገብ እንዲመረመርና ክፉኛ በተጎዳችው ከተማ መልሶ ግንባታ እንዲደረግ ጠይቀዋል።
በርካታ ባለሞያዎችና የረድኤት ድርጅቶች የሊቢያ የጎርፍ አደጋ መቀልበስ ይቻል ነበር ብለዋል።
በተለይም አደጋውን በመተንበይ አስቀድሞ የነፍስ አድን ስራ መሰራት ነበረበት በማለት የመንግስትን ቸልተኝነት ጠቁመዋል።
ምስራቅ ሊቢያ በመንግስታቱ ድርጅት እውቅና ካለው የትሪፖሊ መንግስት በተለየ አስተዳደር ይመራል።