300 የአየር ኢላማዎችን የመለየት ችሎታ ያለው የሩሲያው “በራሪ ራዳር”
“ዶራ” አውሮፕላን በ600 ኪ.ሜ ርቀት ውስጥ የአየር ኢላማዎችን በመከታተል ለተዋጊ ጄቶች መረጃ ይሰጣል
ሩሲያ “ዶራ” አወሮፕላን አካል ውስጥ ወርቅ የተጠቀመች ሲሆን፤ ለምን የሚለው አነጋጋሪ ሆኗል
የሩሲያ አየር ኃይል አለኝ ብሎ ከሚተማመንባቸው ውስጥ በራሪው ራዳር የሚል ቅ ጽል ስም የተሰጠው “ዶራ” የጦር አውሮፕላን አንዱ እና ዋነኛው ነው።
የሩስያ በራሪ ራዳር “ዶራ” የጦር አውሮፕላን ዘመናዊና የተሻሻለው የA-500 ስሪት ሲሆን፤ ትዕዛዝ እና የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ አውሮፕላን መሆኑን የሩስያ መገናኛ ብዙሃን ዘገባ ያመለክታል።
በራሪው ራዳር “ዶራ” በአንድ ጊዜ ከ300 በላይ የአየረ ላይ ኢላማዎችን የመለየት እና የመከታተል አቅም ያለው መሆኑ ተነግሯል።
“ዶራ” አውሮፕላ በ600 ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ የአየር ኢላማዎችን በመከታተል እና በመለየት ተዋጊ ጄቶችን ወደ ኢላማዎቹ የመላክ አቅም ያለው መሆኑም መረጃዎች ይጠቁማሉ።
"በራሪው ራዳር" ለሩሲያ ተዋጊ ተዋጊ ጄት አብራሪዎች ብዙ ጠቀሜታ አለው የተባለ ሲሆን፤ የሩሲያ አየር ኃይል የጠላት የአየር ዒላማዎችን ለማጥፋት አስፈላጊ መረጃዎችን በመስጠት ከፍተኛ ግልጋሎት ይሰጣል።
የሩስያ በራሪ ራዳር “ዶራ” የወርቅ ሽፋኖች
በራሪው ራዳር “ዶራ” የጦር አውሮፕላን ላይ በርካቶችን ያስገረመው ሚስስጥራዊው የወርቅ ሽፋን እንደሆነ ተነግሯል።
“ዶራ” የጦር አውሮፕላን የጋናው የመስታውት መግጠሚያ በጎን እና በላላይኛው ክፍል በወርቅ የተለበደ መሆኑን የሩሲያ ጦር መረጃዎች ያመለክታል።
እንደ ሩሲያ ጦር መረጃዎች ላይ የተለበዱት ወርቆች አብራሪዎችን ከኤሌክትሮ ማግኔቲክ ጨረር ተጋላጭነት ለመከላከል በማለም የተደረገ መሆኑ ተነግሯል።