አረብ ኢሚሬትስና ግብፅ 10 ጊጋ ዋት የንፋስ ሃይል ማመንጫ ለመገንባት ስምምነት ተፈራረሙ
ስምምነቱ የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት ሞሃድ ቢን ዛይድና የግብፅ ፐሬዝዳንት አልሲሲ በተገኙበት ነው የተካሄደው
አረብ ኢሚሬትስ በግብፅ የምትገነባው የንፋስ ኃይል መመንጫ በዓለም ላይ ካሉት ትላልቅ የንፋስ ሃይል ፕሮጀክቶች አንዱ ይሆናል
አረብ ኢሚሬትስ እና ግብፅ 10 ጊጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው ግዙፍ የንፋስ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በግብፅ ለማቋቋም ስምምነት ተፈራርመዋል።
የፊርማ ስነ ስርዓቱ የአረብ ኤሚሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ ሞሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን እና የግብፁ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ አልሲሲ በተገኙበት በግብጽ ሻርምአል ሼክ ተካሂዷል።
በስምምነቱ የሃሰን አላም ኩባንያ እና የግብፅ መንግስት በግብፅ 10 ጊጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው ግዙፍ የንፋስ ሃይል ማመንጫ የሚገነቡ ሲሆን፤ የባህር ላይ የንፋስ ሃይል ፕሮጀክትን በአለም ላይ ካሉት ትላልቅ የንፋስ ሃይል ፕሮጀክቶች አንዱ ይሆናል ተብሏል።
አረብ ኢሚሬትስ በኩል ስምምነቱን የፈረሙት የኢንዱስትሪ እና የረቀቁ ቴክኖሎጂዎች ሚኒስትር ዶ/ር ሱልያን ቢን አህምድ አል ጃብር፤ የ 10 ጊጋ ዋት አቅም ያለው ይህ ግዙፍ የባህር ላይ የንፋስ ሃይል ፕሮጀክት ይፋ ማድረጉ ኤምሬትስ እና ግብፅ በታዳሽ ሃይል መስክ ያላቸውን ቁርጠኝነት ያረጋግጣል ብለዋል።
አክለውም “ፕሮጀክቱ አረብ ኤሚሬትስ በአህጉራዊ እና በአለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት እርምጃን በማንቃት የመሪነት ሚናዋን አጠናክራ መቀጠሏንያረጋገጠ መሆኑንም ዶ/ር ሱልጣን አስታውቀዋል
የንፈስ ኃይል ማመንጫው ግንባታ ሲጠናቀቅ በዓመት 47,790 ጊጋ ዋት ንፁህ ሃይል ያመርታል ይታበለ ሲሆን፤ ይህም 23.8 ሚሊዮን ቶን የካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀትን ለማስቀረት አስተዋፅኦ ያደርጋል።
አዲሱ የባህር ዳርቻ የንፋስ ሃይል ማመንጫ ግብፅ 5 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ዓመታዊ የተፈጥሮ ጋዝ ወጪን እንደሚያስቀርላትም ተነግሯል።
ፐሮጀክቱ በግንባታ ወቅት ለ100 ሺህ ሰዎች የስራ እድልን ይፈጥራል የተባለ ሲሆን፤ በዚህም በግንባታው ደረጃ ቀጥታ ለ30 ሺህ ሰዎች በቀጥታ፤ 70 ሺህ የሚጠጉ ሰዎችን በተዘዋዋሪ ከፕሮጀክቱ የስራ እድል ተጠቃሚ ይሆናሉ።
በተጨማሪም የጣቢያው የግንባታ ስራ ከተጠናቀቀ በኋላ ወደ 3 ሺህ 200 ለሚጠጉ ሰዎች በመደበኛ እና በጥገና የስራ እድል ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል።