የፓኪስታን የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር ኢምራን ካሃን ከግድያ ሙከራ ከተረፉ በኋላ የፖለቲካ ጉዟቸውን ጀመሩ
ካሃን ግድያውን በማሴር የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሼህባዝ ሻሪፍን ወንጅለዋል
የፓኪስታን መንግስት የቀድሞውን ጠቅላይ ሚንስትር ክሱን አጥብቆ አስተባብሏል
የፓኪስታን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካን ባለፈው ሳምንት ከተደረገባቸው የግድያ ሙከራ ካገገሙ በኋላ የፖለቲካ እንቅስቃሴያቸውን ዳግም ጀምረዋል።
ኢምራን ካን ለደጋፊዎቻቸው ወደ ዋና ከተማዋ ኢስላማባድ የሚያደርጉትን “ረጅም ጉዞ” እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።
በተንቀሳቃሽ ምስል ባስተላለፉት መልዕክት ካን “ለእውነተኛ ነፃነት” ትግሉን ለመቀጠል ቃል ገብተዋል።
የፓኪስታን ቴህሬክ ኢ-ኢንሳፍ ፓርቲ ተኩስ በተደረገበት ዋዚራባድ ቦታ ላይ ሰልፍ እንዲያደርጉ ደጋፊዎቻቸው እገዳዎችን እንዲያነሱ አሳስበዋል።
"ራዋልፒንዲ እደርሳለሁ። ሁላችሁም እንድትመጡ እና ከእኛ ጋር እንድትዘምቱ እጋብዛችኋለሁ ምክንያቱም የነገ የሀገር እና የልጆቻችሁ እጣፈንታ ጉዳይ ነው" ማለታቸውን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኸን የሆነው ዘ ኔሽን ዘግቧል።
ኢምራን ካን በሚያዝያ ወር በእንደራሴዎች ድምጽ ከስልጣን ከተነሱ በኋላ ምርጫ እንዲደረግ ለመግፋት በተካሄደ ሰልፍ ላይ ነበር በጥይት የተመቱት። በዚህ ጥቃት የአንድ ሠው ህይወት ሲጠፋ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር በተቀናቃኞቻቸው የተደረገ “የግድያ ሙከራ” መሆኑን ተናግረዋል።
ባለፈው ሳምንት ፖሊስ ይፋ ባደረገው ሪፖርቱ መሃመድ ናቪድ የተባለ ግለሰብ የዋዚራባድን ጥቃት ፈጽሟል። ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር የዋለው በቦታው ላይ በካን ደጋፊ ከተጠለፈ በኋላ ነውም ተብሏል።
ካን ቢያንስ ሁለት ተኳሾች ባለፈው ሳምንት “የታቀደውን” ጥቃት ፈጽመዋል ሲሉ የፖሊስን ሪፖርት ውድቅ አድርገዋል።
ካሃን የፓኪስታን ጠቅላይ ሚንስትር ሼህባዝ ሻሪፍ፣ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትር ራና ሳኑላህ እና ሜጀር ጀነራል ፋይሰል ናሲር ግድያውን በማሴር በኃይማኖታዊ አክራሪ ላይ አላከዋል ብለዋል።
ይህ እቅድ እንደተዘጋጀ እና የኃይማኖት አክራሪዎች እንደሚወቅሱበት አስቀድሜ ከወራት በፊት ተናግሬ ነበር ብለዋልም።
ይሁን እንጂ የፓኪስታን መንግስት እና ወታደራዊ ኃይሎች ክሱን አጥብቀው አስተባብለዋል። ተኳሹ ጥቃቱን በኃይማኖታዊ መሰረት ያደረገ "በራስ ተነሳሽነት ነው" ብለዋል።ካሃን ግድያውን በማሴር የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሼህባዝ ሻሪፍን ወንጅለዋል