አውሮፕላኖች በቦሌ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እያረፉ አይደለም - የኢትዮጵያ አየርመንገድ
አየርመንገዱ ባወጣው መግለጫ ጭጋጋማው የአየር ሁኔታ አውሮፕላኖች በሌሎች ማረፊያዎች እንዲያርፉ አስገድዷል ብሏል
የአየር ሁኔታው በረራዎችን ማስተጓጎሉን በመጥቀስም ለመንገደኞች ይቅርታ ጠይቋል
በአዲስ አበባ በዛሬው እለት የተከሰተው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ በረራዎችን ማስተጓጎሉ ተነገረ።
የኢትዮጵያ አየርመንገድ ባወጣው መግለጫ በአየር ሁኔታው ምክንያት ከጠዋት 3 አካባቢ ጀምሮ የአየር መንገዱ የበረራ አውሮፕላኖች በቦሌ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እያረፉ እንደማይገኙ ጠቁሟል።
አየርመንገዱ አውሮፕላኖች በሌሎች አውሮፕላን ማረፊያዎች ለማረፍ መገደዳቸውን ቢጠቅስም የት አካባቢ እያረፉ ስለመሆኑ ግል አልጠቀሰም።
ጭጋጋማው የአየር ሁኔታ የአገር ውስጥና የዓለም አቀፍ የጠዋት የመነሻ በረራዎች ላይ ተጽእኖ ማሳደሩን አየርመንገዱ ባወጣው መግለጫ አመላክቷል።
“ተሳፋሪዎች በበረራ እቅዳቸው ላይ ያገጣማቸውን መስተጓጎል መፍትሔ እንዲያገኝ አስፈላጊውን ሁሉ አማራጮች እየወሰደ ይገኛል”ም ብሏል።
የስታር አሊያንስ አባሉ የኢትዮጵያ አየርመንገድ ተሳፋሪዎች ላጋጠማቸው የጉዞ መስተጓጎል ይቅርታን ጠይቋል።