ቅዳሜ እለት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ከተቃጣባቸው የመግደል ሙከራ መትረፋቸው ይታወሳል
በሰዎች እጅ የተገደሉ እና የመግደል ሙከራ የተደረገባቸው የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች።
አሜሪካ እንደ ሀገር ከተመሰረትችበት 1776 ወዲህ በተለያዩ ፕሬዝዳንቶች እና ዕጩዎች ላይ በርካታ የግድያ ሙከራዎች ተደርገዋል፡፡
ከነዚህ መካከል አራት የሚሆኑት ሲገደሉ 8 የሚሆኑት ደግሞ ከግድያ ሙከራ አምልጠዋል፡፡
የጥቁሮችን ነጻነት ያወጀው እና የባርያ ንግድን ያስቀረው 16ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት አብርሀም ሊንከን በሰዎች እጅ ከተገደሉ የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ቀዳሚው ነው፡፡
ለጥቁሮች በሰጠው መብት የተነሳ በ1865 በዋሽንግተን ትያትር እየተመለከተ በነበረበት ወቅት ከጀርባው በተተኮሰበት ጥይት ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል፡፡
ስልጣን በያዘ በስድስተኛው ወር የተገደለው 20ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጄምስ ጋርፊልድ ሲሆን በ1881 ወደ ኒው ኢንግላንድ ለመጓዝ ባቡር እየተሰፋረ እንዳለ በጥይት ተመቶ ህይወቱ አልፏል፡፡
25ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ማክኔሊ እና 35ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ በተመሳሳይ በተቃጣባቸው ጥቃት ከተገደሉ የአሜሪካ መሪዎች መካከል ሲሆኑ ፤ በተለይ የጆን ኤፍ ኬኔዲ አሟሟት ለበርካታ ጊዜያት ሲወዛግብ እና ሲያነጋግር የቆየ የግድያ ወንጀል እንደነበር ይታወሳል፡፡
ፍራንክሊን ሩዝቬልት ፣ ሃሪ ትሩማን ፣ ጄራልድ ፎርድ ፣ ሮናልድ ሬገን ፣ ጆርጂ ደብሊው ቡሽ ፣ ቴዎዶር ሩዝቬልት እና ዶናልድ ጥራምፕን ጨምሮ ሌሎችም የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ እጩዎች ከተቃጣባቸው የግድያ ሙክራ በህይወት ሊተርፉ ችለዋል፡፡