ትራምፕ በሰሜን ካሮላይና ማሸነፋቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ ምርጫው የማሸነፍ እድላቸው ወደ 89 በመቶ ከፍ አለ
16 ወኪል መራጮች ያሉባትን ኖርዝ ካሮላይናን በማሸነፍ የትራም እድል ከፍ ቢልም አሸናፊውን ለማወቅ እስከመጨረስ ሰአት ድረስ መጠበቅ ግድ ይላል
ትራምፕ ኢኮኖሚን ዋነኛ አጀንዳቸው ያደረጉ ዜጎችን 80 በመቶ ድምጽ ማግኝታቸው ተሰምቷል
የሪፐሊካኑ ዕጩ ዶናልድ ትራምፕ የምርጫውን ውጤት ለመወሰን ያግዛሉ ከሚባሉ ወሳኝ ግዛቶች መካከል አንዱ በሆነው የኖርዝ ካሮላይና ግዛት ማሸነፋቸውን አረጋገጡ፡፡
ይህን ተከትሎም ትራምፕ ወደ ፕሬዝዳንትነት ለመመለስ የሚያስችላቸውን ትኬት አግኝተዋል እየተባለ ይገኛል፡፡
የትራምፕ የኖርዝ ካሮላይና ድል አጠቃላይ የማሸነፍ እድላቸውን ወደ 89 በመቶ ከፍ እንዳደረገው ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ሆኖም በቀጠለው ትንቅንቅ የ6 ግዛቶች ድምጽ የሚጠበቅ ሲሆን አሁን ባለው የምርጫ ውጤት ሁለቱም ዕጩዎች ካሏቸው 269 የወኪል መራጮች ድምጽ( Electoral College votes) ትራምፕ 230ውን ሲያሸንፉ ሃሪስ በ169 ድምጽ እየተከተሉ ይገኛሉ፡፡
አሸናፊው ቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት መሆኑን ለማረጋገጥ 270 ድምጾችን ማግኝት ይኖርበታል፡፡
የምርጫ ተንታኞች ትራምፕ ሌላኛዋ ከፍተኛ የወኪል መራጮች ድምጽ እንዳላት በሚነገርባት ጆርጂያ የማሸነፍ ከፍተኛ ግምት ሰጥተዋቸዋል፡፡
ተንታኞቹ እንዳሉት በግዛቷ ድል ከቀናቸው የትራምፕን በ17 ግዛቶች ማሸነፍ የሚያረጋግጥ ይሆናል ፡፡
ይህም በቀሪዎቹ ወሳኝ ግዛቶች ፔንሴልቫኒያ ፣ ሚቺጋን እና ዊስኮንሲን ከትራምፕ ያነሰ ድምጽ ያገኙትን ካማላ ሃሪስ የማሸነፍ እድል የሚያጠበው እንደሆነ ነው የተነገረው፡፡
የኢኮኖሚ መሻሻልን ዋነኛ አጀንዳቸው ያደረጉ አሜሪካውያን ለትራምፕ ድምጻቸውን እየሰጡ ሲሆን በአንጻሩ ካማላ ሃሪስ በሂስፓኒክ ወይም ላቲኖ አሜሪካን መካከል 53 በመቶ ድጋፍ ማግኝታቸው ተሰምቷል፡፡
በመላ ሀገሪቱ ካሉት መራጮች 45 በመቶ የሚሆኑት የቤተሰባቸው የፋይናንስ ሁኔታ ከአራት ዓመታት በፊት ከነበረው አሁን ላይ ችግር ውስጥ ይገኛል፤ በዚህም ለትራምፕ 80 በመቶ ሀሪስን ድግሞ 17 በመቶ መራጮች ለኢኮኖሚ መፍትሄ ናቸው ብለው ድጋፋቸውን ሰጥተዋል፡፡
በሌላ በኩል ከዚህ ቀደም የዴሞክራቶች ከፍተኛ ድጋፍ የነበረባቸውን ዌስት ቨርጂኒያ እና ኦሀዮ በርካታ ድምጽ ያገኙት ሪፐብሊካኖች የሴኔቱን መቀመጫ በበላይነት ማሸነፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡