እጩ ፕሬዝደንት ካማላ ሀሪስ የመጠጥ ዋጋን ዝቅ እንደሚያደርጉ ቃል ገቡ
ከአልኮል መጠጦች ባለፈ የምግብ እና መጠጥ ዋጋ ዝቅ እንዲል የሚያስችሉ ስራዎችን እንደሚከተሉ በምረጡኝ ቅስቀሳ ወቅት ተናግረዋል
የዶናልድ ትራምፕ ምርጫ ቅስቀሳ ቡድን ግን የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና ካማላ ሀሪስ ጥምረት ያመጡት ሀሳብ የማይሳካ ነው ሲል አጣጥሏል
እጩ ፕሬዝደንት ካማላ ሀሪስ የአልኮል መሸጫ ዋጋን ዝቅ እንደሚያደርጉ ቃል ገቡ፡፡
የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው አሜሪካ የፊታችን ሕዳር ወር ላይ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለማድረግ ቀነ ቀጠሮ ይዛለች፡፡
በዚህ ምርጫ ላይ ዶናልድ ትራምፕ ከዲሞክራት ፓርቲ እንዲሁም የወቅቱ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ካማላ ሀሪስ ደግሞ ሪፐብሊካን ፓርቲን ወክለው ለፕሬዝዳንትነት እንደሚወዳደሩ ተረጋግጧል፡፡
ሁለቱም በየራሳቸው የምርጫ ቅስቀሳ ላይ ያሉ ሲሆን ካማላ ሀሪስ ከሰሞኑ በካሊፎርኒያ በተዘጋጀ አንድ መድረክ ላይ እንዳሉት የአልኮል መጠጦች ዋጋን ዝቅ ለማድረግ እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል፡፡
እጩ ፕሬዝዳንቷ አክለውም ከግሮሰሪ ምርቶች ባለፈ የምግብ ምርቶችን ጨምሮ ሌሎች መሰረታዊ ፍጆታዎች ዋጋ እንዲቀንስ ማድረግ ከተመረቁበት ጊዜ ጀምሮ የ100 ቀናት እቅዳቸው አካል እንደሚሆንም ተናግረዋል ሲል ፖለቲኮ ዘግቧል፡፡
ይሁንና የዶናልድ ትራምፕ ምርጫ ቅስቀሳ ቡድን ግን የካማላ ሐሪስን እቅድ የማያሳካ እና ውሸት ነው ሲል አጣጥሏል፡፡
አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንድታደርግ ከግብጽ ጉቦ የተቀበሉት ሴናተር ቦብ ሜነንዴዝ መጨረሻ ምን ሆነ?
ዘገባው አክሎም የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና ሐሪስ ጥምረት አስተዳድር የአሜሪካንን ኢኮኖሚ በእጅጉ የጎዳ እጩ ፕሬዝዳንቷም ለኢኮኖሚው ትኩረት እሰጣለሁ ማለታቸው ሐሰት ነው ሲልም የትራማፕ ቡድን መተቸቱ ተገልጿል፡፡
የዶናልድ ትራምፕ ቡድን ከካማላ ሀሪስ ቡድን በኢኮኖሚ ጉዳዮች የተሻለ ሊሰራ እንደሚችል የቅድመ ምርጫ ጥናት ውጤቶች ያሳያሉ፡፡
ዲሞክራቶች ይህን ብልጫ ለመቀልበስ በቀጣይ የኢኮኖሚ ጉዳዮች ዋነኛ የምርጫ ቅስቀሳ አጀንዳ ሊሆን እንደሚችልም ተገልጿል፡፡