ጋዜጠኛው በቅርቡ ከመንግስት ጋር ግንኙነት ያለው የሚዲያ ተቋም የገንዘብ ማጭበርበር ጉዳይ ሲዘግብ ነበር ተብሏል
ታዋቂው የካሜሮን ጋዜጠኛ "የተቆራረጠ አካል" ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ከተጠለፈ ከአምስት ቀናት በኋላ በዋና ከተማዋ ያውንዴ አቅራቢያ ተገኝቷል።
የሚዲያ ተሟጋቾች የማርቲኔዝ ዞጎ መጥፋት እና ሞት በአፍሪካ ያለውን የጋዜጠኞች ህይወት አደጋ ተጨማሪ ምልክት አድርገው ወስደውታል።
አምፕሊቱድ ኤፍ ኤም የተባለ የግል ሬዲዮ ጣቢያ ዳይሬክተር የነበረው ጋዜጠኛው በፈረንጆቹ ጥር 17 መታገቱ ታውቋል።
ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን እንዳለው ዞጎ በቅርቡ ከመንግስት ጋር ግንኙነት ያለው የሚዲያ ተቋም ላይ በገንዘብ ማጭበርበር ጉዳይ አየር ላይ ሲያወራ ነበር ብሏል።
የካሜሩን የጋዜጠኞች የስራ ማህበር ባወጣው መግለጫ "የካሜሩን መገናኛ ብዙኸን አንድ አባሉን አጥቷል፤ የጥላቻ እና የአረመኔነት ሰለባ ሆኗል" ማለቱን ሮይተርስ ዘግቧል።
ካሜሮን ጋዜጠኞችና የሚዲያ ነፃነት በአምባገነን መንግስታት ስጋት ላይ ወድቀዋል ብለው ቅሬታቸውን ከሚያሰሙባቸው የአህጉሪቱ በርካታ ሀገራት አንዷ ናት።