ታዋቂዋ የኒው ዮርክ ዶክተር ራሷንና ልጇን መግደሏ ተገለጸ
በዶክተሯ ይታከሙ የነበሩ ታካሚዎች በድርጊቱ ደንግጠዋል ተብሏል
ዶክተር ክሪስታል ካሴታ ታዋቂ የካንሰር ሐኪም ነበሩ
ታዋቂዋ የኒው ዮርክ ዶክተር ራሷንና ልጃን መግደሏ ተገለጸ።
የ40 ዓመቷ ዶክተር ካትሪን በኒውዮርክ ሆስፒታል ታዋቂ የካንሰር ሐኪም ነበረች።
ሐኪሟ የአራት ዓመት ከመንፈቅ ሴት ልጇን በሽጉጥ ተኩሳ ከገደለቻት በኋላ ራሷ ላይ ተኩሳ እንደገደለች ኒውዮርክ ፖስት ጋዜጣ ዘግቧል።
እንደዘገባው ከሆነ ዶክተር ካትሪን ለምን ልጇን እና ራሷን እንደገደለች ፖሊስ ያልገለጸ ሲሆን ምርመራው እንደቀጠለ ነው ተብሏል።
ዶክተር ካትሪን ባሳለፍነው ቅዳሜ ምሽት በመኖሪያ ቤቷ ውስጥ ፈጽመዋለች በተባለው በዚህ ጥቃት ባለቤቷ ለሌላ ስራ ከቤት ውጪ እንደነበር ተገልጿል።
ዶክተር ካትሪን በተለይም በኮቪድ-19 ወቅት ራሷን ለከፋ ጉዳት አጋልጣ ታካሚዎችን ስትረዳም ነበር ተብሏል።
ዶክተር ክሪስታል ባንድ ወቅት እንደተናገረችው የ8ኛ ክፍል ተማሪ እያለች የእናቷ የቅርብ ጓደኛ በካንሰር ሕመም ተጠቅታ መሞቷን ተከትሎ ሐኪም የመሆን ፍላጎት እና ጥረት የጀመረችው።
በስራ ባልደረቦቿ እና ደንበኞቿ ተወዳጅ የነበረችው ዶክተር ክሪስታል ምንም አይነት የሀዘን ስሜት አልያም መከፋት ታይቶባት እንደማይታወቅም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።
የኒውዮርክ ፖሊስ በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ ምርመራዎችን በማድረግ ላይ ሲሆን ፖሊስ በምርመራው ተጨማሪ የሞት ምክንያት የማግኘት እድሌ አነስተኛ ነው ብሏል።