ከፍተኛ የምግብ ብክነት ያለባቸው 10 ሀገራት
ከ309 ሚሊየን በላይ ሰዎች በረሃብ ውስጥ በሚኖሩባት ምድር ከ930 ሚሊየን ቶን በላይ ምግብ በአመት ይባክናል
ከአጠቃላይ የምድር አመታዊ የምግብ ምርት አንድ ሶስተኛው በተለያዩ ሁኔታዎች እንደሚባክን መረጃዎች ያሳያሉ
የምግብ ብክነት አንገብጋቢ ከሚባሉ የአለም ችግሮች መካከል አንዱ ነው።
በየአመቱ ከ931 ሚሊየን ቶን በላይ ምግብ በየአመቱ በአለም አቀፍ ደረጃ ይባክናል፡፡ ይህ መጠን በ2019 ከነበረበት 1.3 ቢሊየን ቶን ቅናሽ ቢያሳይም ብክነቱ አሁንም በከፍተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ 783 ሚሊየን ሰዎች የምግብ ድጋፍ ይሻሉ፤ ከእነዚህ መካከል በ72 ሀገራት የሚኖሩ 309 ሚሊየን ሰዎች ስር በሰደደ ረሃብ ውስጥ የሚኖሩ ናቸው፡፡
ከአለም አጠቃላይ የምግብ ምርት አንድ ሶስተኛው በአመት የሚባክን ሲሆን የሚባክነው ምግብ በተለያዩ የአለም ክፍሎች በረሃብ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን በበቂ መመገብ የሚችል ነው፡፡
በገንዘብ ሲተመን ወደ አንድ ትሪሊን ዶላር እንደሚጠጋ ለሚገመተው ብክነት የመኖርያ ቤቶች ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛሉ፡፡ መኖርያ ቤቶች 61 በመቶ የብክነት ድርሻ ሲኖራቸው፣ የምግብ መሸጫዎች ደግሞ 26 በመቶ ድርሻ ይይዛሉ፡፡
በቢሊየን የሚቆጠር ህዝብ ያላቸው ቻይና እና ህንድ በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ምግብ አባካኞች ሲሆኑ በከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጫና እና የኑሮ ውድነት ውስጥ የምትገኝው ናይጄሪያ ደግሞ ሶስተኛዋ ናት፡፡