ተጨዋቿን የሳሙት የስፔን እግርኳስ ኃላፊ ይቅርታ ጠየቁ
በድርጊቱ የተቆጡት የስፔን ሁለተኛዎ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኃላፊው ከስልጣን በፍቃዳቸው እንዲለቁ ጥሪ እያቀረቡ ናቸው
ሩቢያልስ በፌደሬሽኑ በኩል ባወጣው የቪዲዮ መግለጫ"በእርግጠኝነት ተሳስቻለሁ፤ ይህን ማመን አለብኝ" ብሏል
የሰፔን እግር ኳስ ፌደሬሽን ኃላፊ የዓለም ዋንጫ ድልን እያከበሩ በነበረበት ሰአት የተጫዋች ጀኒ ሄርሞሶን ከንፈር ሳታስብበት መሳማቸው ቁጣ መቀስቀሱን ተከትሎ ለድርጊታቸው ይቅርታ ጠይቀዋል።
በድርጊቱ የተቆጡት የስፔን ሁለተኛው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኃላፊው ከስልጣን በፍቃዳቸው እንዲለቁ ጥሪ እያቀረቡ ናቸው።
ድርጊቱ የተፈጸመው የፌደሬሽኑ ፕሬዝደንት ሊዊስ ሩቢያልስ በአለም ዋንጫ ፍጻሜ ውድድር እንግሊዝን 1-0 ላሸነፈው የስፔን ቡድን የወርቅ ሜዳሊያ በሰጡበት ወቅት መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
ሩቢያልስ በፌደሬሽኑ በኩል ባወጣው የቪዲዮ መግለጫ"በእርግጠኝነት ተሳስቻለሁ፤ ይህን ማመን አለብኝ" ብሏል።
የስፔን ብሔራዊ ቡድን ከአውስትራሊያው ድል ተመልሶ ሰኞ ማታ ስፔን ሲደርሱ ሩቢያልስ ስለሁኔታው ተጠይቆ መልስ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆነም።
"አሁን ጊዜው ድልን የማጣጣም ነው። የአለም ዋንጫ አሸንፈናል።" ብሏል ሩቢያልስ።
ሄርሞሶ የመሳም ድርጊት ከተፈጸመባት በኋላ ለቡድኑ አባት"ድርጊቱን አልወደድኩትም" ብላ መናገሯን የሚገልጽ ቪዲዮ በተለያዩ ሚዲያዎች ዩቲዩብ እና ኢንስታግራም አካውንቶች ተጋርቷል።
ነገርግን ቆየት ብላ ለስፔን ዜና አገልግሎት በላከችው መግለጫ ድርጊቱን አቃላዋለች።
ሄርሞሶ እንደገለጸችው"የዓለም ዋንጫ በማንሳት በተፈጠረ ደስታ ምክንያት የተፈጠረ የጋራ ስሜት ነው"።
"ፕሬዝደንቱ እና እኔ መልካም የሚባል ግንኙነት አለን፤ ለሁላችንም የሚያሳየው ፀባይ እንከንየለሽ ነው። ይህ ድርጊቱ የተፈጥሯዊ ፍቅር እና ክብር ማሳያ ነው" ብላለች ሄርሞሶ።
ከጨዋታ በኋላ በወጡ ቪጂዮዎች ሩቢየልስ ሜዳሊያ በሰጡቀት ወቅት ሌሎች ተጨዋቾችን ጉንጫቸው ላይ ሲስም ወይም ሲያቅፍ ታይቷል።
ሩቢያልስ በጨዋታው ወቅት በስቴዲየም ከስፔን ንግስት እና ከአንድ ሴት ልጇ ጎን ተቀምጦ ድሉን በጥልቅ ደስታ አክብሯል።
የፆታ ጉዳይ በስፔን እንደቀላል የሚታይ ርዕስ አይደለም። በሶሺያሊስት ርዕዮተ አለም የሚመራው የስፔን መንግስት በፆታ ጉዳይ የህግ ማሻሻያዎችን እያደረገ ይገኛል።